1በድጋሚ የእግዚአብሔር ልጆች በያህዌ ፊት ራሳቸውን በሚያቀርቡበት ቀን ፥ ሰይጣንም ደግሞ አብሮ መጣ።
2እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦“ ከወዴት እየመጣህ ነው?” አለው። ሰይጣንም ለእግዚአብሔር ሲመልስ፦ “ምድርን ሁሉ ዞርሁ፥ በእርስዋም ላይ ወዲህና ወዲያ ተመላልሼ መጣሁ” ብሎ አለ።
3እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦”በውኑ ባሪያዬን ኢዮብንስ ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ በደል የማይገኝበት ትክክለኛ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም። ምንም እንኳ ያለምክንያት በእርሱ ላይ በከንቱም ጥፋት እንዲመጣበት ግፊት ብታደርግብኝም ፥ እርሱ ግን እስከ አሁን በታማኝነቱ ጸንቷል“ አለው።
4ሰይጣንም መልሶ እግዚአብሔርን፦ “ቆዳ በርግጥ ስለ ቆዳ ነው፤ ሰው ያለውን ነገር ሁሉ ሕይወቱን ለማዳን ሲል ይሰጣል” አለው።
5ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ሰውነቱ ላይ ጉዳት ብታደርስ ፊተ ለፊት ይክድሃል” አለው።
6እግዚአብሔም ሰይጣንን፦” ሕይወቱን ብቻ ተው፤ እነሆ፥ እርሱ በእጅህ ነው“ አለው።
7እናም ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ። ኢዮብንም ከውስጥ እግሩ እስከ ራስ ጸጉሩ ድረስ በሚያሰቃይ ቍስል መታው።
8ኢዮብም ሰውነቱን ለመፋቅ የሸክላ ስባሪ ወሰዶ በአመድ ላይ ተቀመጠ።
9በኋላም ሚስቱ ፦”እስከ አሁን በታማኝነት ጸንተሃል እንዴ? እግዚአብሔርን እርገምና ሙት“ አለችው።
10እርሱ ግን መልሶ”አንቺ እንደ ሰነፍ ሴቶች ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ብቻ እንጂ ክፉን አንቀበልም ብለሽ ነው የምታስቢው? “ አላት። በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ኢዮብ በአፉ ቃል ሐጢያት አላደረገም።
11ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ በሰሙ ጊዜ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ከየስፍራቸው መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ከኢዮብ ጋረ ሊያለቅሱና ሊያጽናኑት በአንድነት ጊዜ አመቻችተው መጡ።
12ከሩቅ ዓይናቸውን አማትረው ሲመለከቱ በትክክል ሊለዩት አልቻሉም፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ እያንዳንዳቸውም ልብሳቸውን ቀደዱ፥ አቧራ ወደ ላይ እየበተኑ ራሳቸው ላይ ነሰነሱ።
13ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት ከእርሱ ጋር መሬት ላይ ተቀመጡ፤ ሕመሙም እጅግ ከባድ እንደነበረ ስላዩ ከእርሱ ጋር አንድ ቃል ለመናገር የደፈረ አልነበረም።