መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ዖጽ በሚባል ምድር ኢዮብ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ኢዮብም በደል የማይገኝበት፤ ትክክለኛ፤ እግዚአብሄርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ሰው ነበረ።
2ለእርሱም ሰባት ወንዶችና ሶስት ሴቶች ልጆች ተወልደውለት ነበር።
3ሰባት ሺህ በጎች፤ ሶስት ሺህ ግመሎች፤ አምስት ሺህ ጥንድ በሬዎችና አምስት ሺህ አህዮች እንዲሁም እጅግ ብዙ ሰራተኞች ነበሩት። ይህም ሰው በምስራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ሰው ነበር።
4ወንዶች ልጆቹም በየተመደበላቸው ተራ በያንዳንዳቸው ቤት ግብዣ ያደርጉ ነበር፤ ሦስቱ እኅቶቻቸውም ከእነርሱ ጋር እንዲበሉና እንዲጠጡ ልከው ይጠሩአቸው ነበር።
5የግብዣቸውም ቀናቶች ሲያበቁ ኢዮብ፦ ያስጠራቸውና ለእግዚአብሔር መልሶ ይቀድሳቸው ነበር።ማልዶ በጠዋት ተነስቶ “ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ረግመው ይሆናል” ብሎ ፤ ለልጆቹ ለእያንዳንዳቸው የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል። ይህንንም ኢዮብ ሁልጊዜ ያደርግ ነበር።
6በኋላም የእግዚአብሔር ልጆች በያህዌ ፊት ራሳቸውን የሚያቀርቡበት ቀን ነበረ ፥ ሰይጣንም ደግሞ ከእነርሱ ጋር መጣ።
7እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦“ ከወዴት እየመጣህ ነው?” አለው። ሰይጣንም ለእግዚአብሔር ሲመልስ፦ “ምድርን ሁሉ ዞርሁ፥ በእርስዋም ላይ ወዲህና ወዲያ ተመላልሼ መጣሁ” አለ።
8እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦”በውኑ ባሪያዬን ኢዮብንስ ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ በደል የማይገኝበት ትክክለኛ ሰው ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም“ አለው።
9ሰይጣንም ለእግዚአብሔር ሲመልስ እንዲህ አለ፦ “ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራው እንዲሁ ነውን?
10በእርሱና በቤቱ ባለውም ነገር ሁሉ ዙሪያ በየአቅጣጫው አጥር አላደረግህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ሐብቱም በምድር ላይ በዝቶአል።
11ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሀብት ሁሉ አውድም ፤ ፊትለፊት ይክድሃል።”
12እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ “እነሆ እርሱ ያለው ነገር ሁሉ በስልጣንህ ስር ነው፥ በእርሱ ላይ ግን ጉዳት እንዳታደርስ” አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ።
13ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ በታላቅ ወንድማቸው ቤት በሚበሉበትና የወይን ጠጅ በሚጠጡበት ቀን እንዲህ ሆነ፤
14መልክተኛ ወደ ኢዮብ መጥቶ፦”በሬዎች እርሻ እያረሱ፥ በአጠገባቸውም አህዮች ተሰማርተው ነበር፤
15የሳባም ሰዎች አደጋ አድርሰው ወሰዱአቸው፥ ሰራተኞቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።
16እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ሌላ መጥቶ፦“ የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወደቀ፥ በጎቹንና ጠባቂዎችን አቃጥሎ በላቸው፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።
17እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ሌላ መጥቶ፦”ከለዳውያን በሦስት ቡድን ተከፍለው በግመሎች ላይ አደጋ ጥለው ወሰዱአቸው ፥ ሰራተኞቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።
18እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ሌላ መጥቶ፦ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት እየበሉና የወይን ጠጅ እየጠጡ ነበር፤
19ታላቅ ነፋስ ከምድረ በዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታውና በልጆቹ ላይ ወደቀ፥ እነርሱም ሞቱ፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።
20ኢዮብም ተነሣ ልብሱንም ቀደደ፥ ራሱንም ተላጨ፥ በምድርም ላይ በፊቱ ተደፍቶ እግዚአብሔርን አመለከ፤
21እንዲህም አለ፦”ከእናቴ ማኅፀን ራቁቴን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን።“
22በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ኢዮብ ሐጢያት አላደረገም፥ በስንፍናም እግዚአብሔርን አልከሰሰም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።