1ሹሐዊው በልዳዶስ ሲመልስ እንዲህ አለ፦
2ወሬህን የምታቆመው መቼ ነው? እስቲ አስብ፥ ከዚያም እኛ እንናገራለን።
3ለምን እንደ እንስሶች ቆጠርኸን? ለምን በአንተ ፊት እንደ ቆሻሻ ሆንን?
4አንተ በራስህ ቍጣ ተወርሰሃል፤ ምድር ለአንተ ሲባል ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ዓለቶች ከስፍራው መወገድ አለባቸው?
5በእርግጥ የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፥ የእሳቱም ነበልባል አያበራም።
6ብርሃን በድንኳኑ ውስጥ ጨለማ ይሆናል፥ በላዩ ያለው መብራትም ይጠፋል።
7የብርታቱም እርምጃ ያጥራሉ፥ የራሱ እቅዶች ወደታች ይጥሉታል።
8በገዛ እግሩ ወደ ወጥመድ ይገባል፥ ወደ ጉድጓድም ውስጥ ይገባል።
9ወጥመድ ተረከዙን ይይዘዋል፥ ወስፈንጠርም በላዩላይ ይሆናል።
10በመሬትም ላይ የሸምቀቆ ገመድ፥ በመንገዱም ላይ ወጥመድ ለእርሱ ተሰውሯል።
11ድንጋጤ በሁሉ አቅጣጫ ያስፈራዋል፥ ከኋላውም ሆነው ያሳድዱታል።
12ብልጥግናው ወደ ራብ ይለወጣል፥ መቅሠፍትም ካጠገቡ ተዘጋጅቶለታል።
13የሰውነቱም ክፍሎች ፈጽመው ይጠፋሉ፤ የሞትም በኵር ልጅም አካል ክፍሎቹን ይበላል።
14ከሚታመንበት ቤት፤ ከተቀመጠበትም ድንኳን ይነቀላል፤ የድንጋጤ ንጉሥ ወደሆነው ወደ ሞት ያመጡታል።
15ዲን በመኖሪያው እንደተበተነ ይመለከታሉ፤ የራሱያልሆኑ ሰዎችም በድንኳኑ ውስጥ ይኖራሉ።
16ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፥ ቅርንጫፉም ከላዩ ይወድቃል።
17መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፥ በመንገድም ላይ ስሙ አይነሳም።
18ከብርሃን ወደ ጨለማ ይወስዱታል፥ ከዚህም ዓለም ያሳድዱታል።
19በሕዝቡ መካከል ልጅ የልጅ ልጅም አይኖረውም፤ ጥቂት የሚቆይበትም ዘመድ እንኳ አያገኝም።
20በአንድ ቀን የሆነበትን ሲያዩ የምዕራብ ሰዎች 、ይደነግጣሉ፥ በምስራቅ የሚኖሩ ሰዎችም ይፈራሉ ።
21በርግጥ የኃጥዕ ቤቶች እንዲህ ናቸው፥ እግዚአብሔርንም የማያውቁ ሰዎች ስፍራ ይህ ነው።