መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 16

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኢዮብም ሲመል እንዲህ አለ፦
2እንደዚህ ያለ ብዙ ነገር ሰምቻለሁ፤ ሁላችሁም የማትጠቅሙ አጽናኞች ናችሁ።
3ከንቱ ቃሎች መጨረሻ የላቸውምን? እንደዚህ ለመመለስ የቻላችሁት ምን ነክቷችሁ ነው?
4እናንተ በእኔ ቦታ ብትሆኑ፤ እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ እኔም ቃላቶችን ሰብስቤ እያቀናበረሁ፥ በማሾፍም በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ እችል ነበር።
5ኦ! በአፌም እንዴት አድርጌ ባበረታታኋችሁ! የከንፈሬም ማጽናናት እንዴት ሃዘናችሁን ባቀለለ ነበር!
6ብናገር ሰቆቃዬ አይቀንስም፤ ከመናገር ዝም ብል እንዴት እገዛ ላገኝ እችላለሁ።
7አሁን ግን እግዚአብሔር አድክመኸኛል፤ ቤተሰቤን ሁሉ አፈራርሰሃል።
8አድርቀኸኛል ይኸውም በላዬ ይመሰክርብኛል፤ የሰውነቴም መጨማተር ምስክር ነው፤ ክሳቴም ተነሥቶ፤በፊቴ ላይ ይመሰክራል።
9እግዚአብሔር በቍጣው ቀደደኝ፥ አሳደደኝም፤ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፤ ይህም ሲሆን ጠላቴ ዓይኑን አፈጠጠብኝ፤
10ሰዎችም በግርምት አፋቸውን ከፈቱ፤ እያላገጡም ጕንጬን ጠፈጠፉኝ፤ በአንድነትም በእኔ ላይ ተሰበሰቡ።
11እግዚአብሔር አመጸኛ ሰዎች አሳልፎ ሰጠኝ፥ በክፉዎችም እጅ ጣለኝ።
12በሰላም ተቀምጬ ነበር፥ እርሱም ሰባበረኝ፤ በርግጥም አንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ ኢላማው አድርጎም አቆመኝ።
13ቀስተኞቹ ከበቡኝ፤ ኵላሊቶቼንም ወጋቸው፥ አላስተረፈኝምም፤ ሐሞቴንም በምድር ላይ አፈሰሰ።
14ከግድግዳዬም ጋር ደጋግሞ አጋጨኝ፤ እንደ ጦረኛ በላዬ ሮጠብኝ።
15በሰውነቴ ላይ ማቅ ሰፋሁ፥ ቀንዴንም በመሬት ላይ ጣልሁት።
16ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፤ በዓይኖቼ ቆብ ላይም የሞት ጥላ አለ፤
17ቢሆንም ግን በእጄ ዓመፅ የለም፤ ጸሎቴም ንጹሕ ነው።
18ምድር ሆይ፥ ደሜን አትሸፍኚ፥ ለቅሶዬም ማረፊያ ቦታ አይኑረው።
19አሁንም ቢሆን፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፥ ለእኔም የሚሟገትልኝ በአርያም ነው።
20ጓደኞቼ ተሳለቁብኝ ነገር ግን አይኖቼ በእግዚአብሔር ፊት እንባን ያፈሳሉ።
21የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ያ በሰማይ ያለው ምስክሬ በእግዚአብሔር ፊት እንዲምዋገትልኝ እጠይቃለሁ!
22ምክንያቱም ጥቂት ዓመታት ካለፉ በኋላ እኔም ወደማልመለስበት ስፍራ እሄዳለሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።