መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በመቀጠልም ኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ፦
2በእርግጥ እናንተ አዋቂ ሰዎች ናቸሁ፤ ጥበብ ከእናንተ ጋር ትሞታለች።
3ነገር ግን እኔ እንደ እናንተው ማስተዋል አለኝ፤ ከእናንተም የማንስ አይደለሁም፤ በእርግጥ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች የማያውቅ ማን ነው?
4እግዚአብሔርን ሲጠራ የሚመልስለት ሰው የነበርሁ እኔ አሁን ለጎረቤቶቼ መሳለቅያ ሆኛለሁ፤ ጻድቅና ነቀፋ የሌለበት የነበርሁ እኔ አሁን ማሾፊያ ሆኛለሁ።
5በደላው ሰው ሃሳብ ውስጥ መከራ የተናቀ ነው፤ እግሩ ለሚሸራተት ሰው ችግሩን ሊጨምርበት ያስባል።
6የዘራፊዎች ድንኳን ይበለጥጋል፥ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ በደህና ተቀምጠዋል፤ የገዛ እጃቸውን አምላካቸው አድርገዋል።
7አሁን ግን እንስሶችን ጠይቁ፥ ያስተምሯችኋል፤ የሰማይንም ወፎች ጠይቁ፥ ይነግሯችኋል።
8ወይም ለምድር ተናገሩ፥ እርስዋም ታስተምራችኋለች፤ የባሕርም ዓሣዎች በግልጥ ይነግሯችኋል።
9ከእነዚህ ሁሉ እንስሳት የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፤ የሕያዋን ሁሉ ህይወት፤
10የሰው ልጆችንም ሁሉ እስትንፋስ በእጁ እንደያዘ የማያውቅ ማን ነው?።
11ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚቀምስ፥ ጆሮ ቃላትን አይለይምን?
12እድሜ በገፉት ዘንድ ጥበብ፥ በዘመን ርዝማኔም ማስተዋል ይገኛል።
13በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ ምክርና ማስተዋልም በእርሱ ዘንድ ይገኛሉ።
14እነሆ፥ እርሱ ያፈርሳል፥ ተመልሶም አይሠራም፤ አንድን ሰው ቢያስር ሊፈታው የሚችል የለም።
15እነሆ፥ ውኆቹን ቢከለክል፥ እነርሱ ይደርቃሉ፤ እንደ ገናም ቢለቃቸው፥ ምድርን ያጥለቀልቃሉ።
16ብርታትና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ የሚስተውና የሚያስተው በእርሱ ስልጣን ስር ናቸው።
17መካሪዎችንም ባዶአቸውን በሃዘን ይሰዳቸዋል፥ ፈራጆችንም አላዋቂ ያደርጋቸዋል።
18የነገሥታትንም የስልጣን ሰንሰለት ይፈታል፥ ወገባቸውንም በመታጠቂያ ልብስ ያስርላቸዋል።
19ይሽራል ባዶአቸውንምይሰዳቸዋል፥ ኃያላንንም ይገለብጣቸዋል።
20የታመኑ ሰዎችንም ንግግረ ያስወግዳል፥ የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስድባቸዋል።
21በአለቆች ላይ ንቀትን ያፈሳል፥ የብርቱ ሰዎችንም ቀበቶ ይፈታል።
22ከጨለማ ውስጥ ጥልቅ ነገሮችን ይገልጣል፥ ከሙታንም ሰፈር የመታየትን ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል።
23ህዝቦችን ብርቱ ያደርጋል፥ ደግሞም ያጠፋቸዋል፤ ህዝቦችንም ያበዛል፥ ደግሞም ወደ ግዞት ይልካቸዋል።
24ከምድር ሕዝብ አለቆች ማስተዋልን ይወስዳል፥ መንገድም በሌለበት ምድረበዳ ያቅበዘብዛቸዋል።
25ብርሃን በሌለበት በጨለማ ይዳክራሉ፤ እንደ ሰካራምም ይንገዳገዳሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።