መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢዮብ 11

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ነዕማታዊውም ሶፋር እንዲህ በሎ መለሰ፦
2ለዚህ ሁሉ ቃል መልስ መስጠት አይገባምን? በንግግር የተማላው ይህ ሰው እንዲያው ይታመናልን?
3ትምክህትህስ ሌሎችን ሁሉ ዝም ያሰኛቸዋልን? ትምህርታችንን ስትሳለቅበት፤ የሚያሳፍርህ ማንም የለምን?
4ለእግዚአብሔር ስትናገር “ትምህርቴ የተጣራ ነው፥በዓይንህም ፊት ነቀፋ የለብኝም” ትላለህ።
5ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ! በአንተም ላይ ከንፈሩን ቢከፍት!
6በማስተዋሉ ታላቅ ነውና፤ የጥበቡን ምሥጢር ምነው ገልጦ ቢያሳይህ! እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ ታውቅ ነበር።
7እግዚአብሔርን መርምረህ ልትረዳው ትችላለህን? ሁሉን የሚችል አምላክን በሙላት ልታውቀው ትችላለህን?
8ነገሩ እንደ ሰማይ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ?
9ርዝመቱ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፥ ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።
10እርሱ በመካከልህ ቢያልፍ፥ የፈለገውን በግዞት ቢዘጋ፥ ለፍርድ የወደደውን ቢጠራ፥ የሚከለክለው ማን ነው?
11እርሱ ሃሰተኛ ሰዎችን ያውቃልና፥ አመጻንም ሲመለከት እንዳላየ ያልፋልን?
12የሜዳ አህያ ሰው በወለደ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ ሞኞች ሊረዱት አይችሉም።
13ነገር ግን ልብህን በትክክል ብታቀና፤ እጅህንም ወደ እግዚአብሔር ብትዘረጋ፥
14በደልንም ከእጅህ እጅግ ብታርቀው፤ በድንኳንህም ኃጢአት ባይኖር፤
15ያን ጊዜ በእርግጥ ያለ እፍረት ቀና ትላለህ፤ ጠንክረህም ትቆማለህ፥ አትፈራምም።
16መከራህንም ትረሳዋለህ፤ እንዳለፎ እንደሔደም ውኃ ታስበዋለህ።
17ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ይበራል፤ ጨለማም ቢኖር እንኳ እንደ ጥዋት ይሆናል።
18ተስፋ ስላለህ ተማምነህ ትቀመጣለህ፤ በዙሪያህ ሁሉ ደኅንነትን ታያለህ፥ በእረፍትም ትቀመጣለህ።
19ለማረፍ ትተኛለህ፥ የሚያስፈራህም የለም፤ ብዙዎችም ያንተን እርዳታ ይሻሉ።
20ነገር ግን የክፉዎች ዓይን ግን ትጨልማለች፤ የሚያመልጡበትም መንገድ የላቸውም፥ ያላቸው ተስፋም የመጨረሻ ትንፋሻቸውን መስጠት ብቻ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።