መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዮሐንስ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ፣ ስሙ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ የአይሁድ ሸንጎ አባል ነበር ፤
2ይህ ሰው በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ «መምህር ሆይ፣ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ክሆነ ሰው በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ማንም ማድረግ ስለማይችል፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር መሆንህን እናውቃለን» አለው።
3ኢየሱስ፣ «እውነት እልሃለሁ፣ ሰው ዳግም ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም» ብሎ መለሰለት።
4ኒቆዲሞስ፣ «ሰው ካረጀ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ወደ እናቱ ማኅፀን ዳግመኛ ገብቶ ሊወለድ ይችላልን?» አለው።
5ኢየሱስ መልሶ፣ «እውነት፣ እውነት፣ እልሃለሁ፣ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
6ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።
7'ዳግም መወለድ አለባችሁ' ስላልሁህ አትደነቅ፤
8ነፋስ ወደ ፈለገው ይነፍሳል፤ ድምፁን ትሰማለህ፣ ነገር ግን ከየት እንደ መጣ፣ ወዴትም እንደሚሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስም የተወለደ ሁሉ እንደዚሁ ነው።»
9ኒቆዲሞስ፣ «ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?» በማለት መለሰ።
10ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ «አንተ የእስራኤል መምህር ሆነህ ሳለ እነዚህን ነገሮች አታውቅምን?
11እውነት፣ እውነት፣ እልሃለሁ፤ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፤ እናንተ ግን ምስክርነታችንን አትቀበሉም።
12ስለ ምድራዊው ነገር ነግሬአችሁ ያላመናችሁ፣ ስለ ሰማያዊው ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?
13ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር፣ ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም።
14ሙሴ እባብን በምድረ በዳ እንደ ሰቀለ፣ እንዲሁ የሰው ልጅ ሊሰቀል ይገባዋል።
15ይህም በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው።
16በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፤
17እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ላይ ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው።
18በእርሱ የሚያምን ሁሉ አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ፣ አሁኑኑ ተፈርዶበታል።
19የፍርዱ ምክንያት ይህ ነው፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለ ነበረ፣ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ፤
20ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤ ድርጊቱም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም።
21እውነትን በተግባር ላይ የሚያውል ሰው ግን ሥራው እግዚአብሔርን በመታዘዝ የተፈጸመ መሆኑ በግልጽ እንዲታይ ወደ ብርሃን ይመጣል።»
22ከዚህ በኋላ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ይሁዳ አገር ሄዱ፤ በዚያ ከእነርሱ ጋር ቆየ፤ ያጠምቅም ነበር፤
23በዚህ ጊዜ ዮሐንስም በሳሌም አቅራቢያ ሄኖን በተባለ ስፍራ ብዙ ውሃ ስለ ነበረ፣ ያጠምቅ ነበር፤ ሰዎችም ወደ እርሱ እየመጡ ይጠመቁ ነበር።
24ምክንያቱም ዮሐንስ ገና በወኅኒ አልተጣለም ነበር።
25ከዚያም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአንድ አይሁዳዊ መካከል ስለ መንጻት ሥርዐት ክርክር ተነሣ።
26ደቀ መዛሙርቱ ወደ ዮሐንስም መጥተው፣ «መምህር ሆይ፣ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው ስለ እርሱ የመሰከርክለት ሰው፣ እነሆ እያጠመቀ ነው፤ ሁሉም ወደ እርሱ እየሄዱ ነው አሉት።»
27ዮሐንስ መልሶ እንዲህ አለ፤ «ሰው ከሰማይ ካልተሰጠው በቀር ምንም ነገር ሊቀበል አይችልም።
28'እኔ ክርስቶስ አይደለሁም' ነገር ግን 'ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ' ማለቴን እናንተ ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ።
29ሙሽሪት ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ አጅቦት ቆሞ የሚሰማው ሚዜው በሙሽራው ድምፅ እጅግ ደስ ይለዋል። አሁን ይህ ደስታዬ ፍጹም ሆኖእል።
30እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባል።
31ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው።
32እርሱ ያየውንና የሰማውን ይመሰክራል፤ ነገር ግን ምስክርነቱን ማንም አይቀበልም።
33ምስክርነቱን የተቀበለ ሰው የእግዚአብሔርን እውነተኝነት አረጋግጧል።
34እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።
35አብ ወልድን ይወዳል ሁሉንም ነገር በእጁ ሰጥቶታል።
36በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ለልጁ የማይታዘዝ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም።»
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።