መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዮሐንስ 14

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1«ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔ ደግሞ እመኑ።
2በአባቴ ቤት ብዙ የመኖሪያ ስፍራ አለ፤ እንደዚያ ባይሆን ኖሮ፣ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁ ብዬ አልነግራችሁም ነበር።
3ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትሆኑ ዳግመኛ እመጣለሁ፣ ወደ ራሴም እወስዳችኋለሁ።`
4ወዴት እንደምሄድ መንገዱን ታውቃላችሁ።»
5ቶማስ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም፣ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?» በማለት ጠየቀው።
6ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ «እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ፤ በእኔ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ አብ ሊመጣ አይችልም።
7እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር። ከአሁን ጀምሮ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል።»
8ፊልጶስ ጌታ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ አብን አሳየን ያ ለእኛ በቂያችን ነው» አለው።
9ኢየሱስ፣ «ፊልጶስ ሆይ፣ ይህን ያህል ጊዜ ከእናንተ ጋር ኖሬ ገና ኣላወቅኸኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል፤ 'እንዴትስ አብን አሳየን' ትላለህ?
10እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እየነገርኋችሁ ያለው ቃል ከራሴ የምናገረው አይደለም፤ ይልቁንስ ይህን ሥራ የሚሠራው በእኔ ውስጥ የሚኖረው አብ ነው።
11እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ሌላው ቢቀር ከምሠራው ሥራ የተነሣ እመኑኝ።
12እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ሥራ እርሱም ይሠራል፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ፣ እኔ ከሠራሁት የሚበልጥ ሥራ ይሠራል።
13አብ በልጁ ይከብር ዘንድ ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።
14ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ፣ እኔ አደርገዋለሁ።
15የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።
16እኔም ለዘላለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ እንዲሰጣችሁ አብን እለምናለሁ።
17እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየው ወይም ስለማያውቀው አይቀበለውም። ይሁን እንጂ፣ ከእናንተ ጋር ስለሚኖርና በውስጣችሁም ስለሚሆን፣ እናንተ ታውቁታላችሁ።
18ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፣ ዳግመኛ ወደ እናንተ እመጣለሁ።
19ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተም ሕያዋን ትሆናላችሁ።
20በዚያን ቀን እኔ በአብ እንዳለሁ፣ እናንተ በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ ታውቃላችሁ።
21ትእዛዜ በውስጡ ያለ የሚያደርገውም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።
22የአስቆሮቱ ያልሆነው ይሁዳም ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ለዓለም ሳይሆን ለእኛ ራስህን የምትገልጠው እንዴት ነው?» ብሎ ጠየቀው።
23ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ «ማንም ሰው ቢወደኝ ቃሌን ይጠብቃል። አባቴም ይወደዋል፣ ወደ እርሱ እንመጣለን፣ መኖሪያችንንም በእርሱ እናደርጋለን።
24የማይወደኝ ማንኛውም ሰው ቃሌን አይጠብቅም። የምትሰሙት ቃል የእኔ ሳይሆን፣ የላከኝ የአብ ቃል ነው።
25በመካከላችሁ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች ልብ እንድትሉ ነግሬአችኋለሁ።
26የሆነ ሆኖ፣ አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ነገር ሁሉ እንድታስታውሱ ያስችላችኋል።
27ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጠው ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፣ አይፍራም።
28'እሄዳለሁ፣ ዳግመኛም ወደ እናንተ እመጣለሁ' ብዬ የነገርኋችሁን ቃል ሰምታችኋል። ከወደዳችሁኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ሊላችሁ ይገባ ነበር፤ ምክንያቱም አብ ከእኔ ይበልጣል።
29ይህ ነገር በሚፈጸምበት ጊዜ ታምኑ ዘንድ አሁን ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ ነገርኋችሁ።
30የዚህ ዓለም ገዥ እየመጣ ስለሆነ ከዚህ በላይ ከእናንተ ጋር መነጋገር አልችልም።እርሱ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን የለውም፡
31ነገር ግን አብን እንደምወድ ዓለም ሁሉ ያውቅ ዘንድ በሰጠኝ ትዕዛዝ መሠረት አብ ያዘዝኝን አደርጋለሁ። ተነሱ ከዚህ እንሂድ»
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።