መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኤርሚያስ 9

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፣ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!
2ሁሉም አመንዝሮች፣ የከዳተኞች ጉባኤ በመሆናቸው ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ የመንገደኞች ማደሪያን ማን በሰጠኝ!
3"አታላይ ቀስታቸው በሆነው በምላሳቸው ሐሰት ተናገሩ፣ ነገር ግን በምድር ላይ በታማኝነት ግሩም አይደሉም። ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉ። እኔንም አላወቁምና፣" ይላል እግዚአብሔር።
4እያንዳንዱ ወንድም ሁሉ ያታልላልና፣ እያንዳንዱ ጎረቤትም ሁሉ ሐሜተኛ ስለሆነ እናንተ ሁሉ ከጎረቤቶቻችሁ ተጠንቀቁ፣ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ።
5እያንዳንዱ ሰውም ሁሉ ጎረቤቱን ያታልላል በእውነትም አይናገርም። ምላሶቻቸው የማታለል ነገሮችን ያስተምራል። በደልንም በማድረግ ይደክማሉ።
6በማታለል መካከል ትኖራላችሁ፣ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፣ ይላል እግዚአብሔር።
7ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ እፈትናቸዋለሁ። እመረምራቸዋለሁ። ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድር ነው?
8ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ያልታመኑ ነገሮችን ይናገራሉ። ከጎረቤቶቻቸው ጋር በአንደበታቸው በሰላም ይናገራሉ፣ በልባቸው ግን ያደቡበታል።
9በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀጣቸውምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንደዚህስ ባለ ሕዝብ ላይ አልበቀልምን?
10ለተራሮች የልቅሶና የዋይታን ዝማሬ እዘምራለሁ፣ ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም የቀብር ዋይታን እዘምራለሁ። ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና። ሰዎችም የየትኛውንም ከብት ድምፅ አይሰሙም። የሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሁሉ ሸሽተው ሄደዋል።
11ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር፣ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይኖርባት ወና አደርጋቸዋለሁ።
12ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ለሌሎች እንዲነግር የእግዚአብሔር አፍ ምን ተናገረው? ምድሪቱስ ስለምን ጠፋች? ማንም እንደማያልፍባት እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተደመሰሰች?
13እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ "በፊታቸው የሰጠኋቸውን ሕጌን ስለተዉ፣ ድምጼንም አልሰሙምና ወይም አልተጓዙበትምና።
14አባቶቻቸው እንዳስተማሯቸው በልባቸውን ምኞት ተመላልሰዋልና፣ በኣሊምን ተከትለዋልና።
15ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የተመረዘንም ውኃ አጠጣዋለሁ።
16እነርሱና አባቶቻቸውም ባላወቁአቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፣ እስካጠፋቸውም ድረስ በበስተኋላቸው ሰይፍን እሰድድባቸዋለሁ።"
17የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ይህንን አስቡ፦ የቀብር አስለቃሾችን ጥሩ፤ ይምጡ። ወደ ብልሃተኛ አልቃሾች ላኩ።
18ይፍጠኑና ዓይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ የለቅሶ ዝማሬን ይዘምሩልን።
19'እንዴት ተበዘበዝን። ቤቶቻችን ስለፈረሱ ምድሪቱንም ትተናልና እንዴት አፈርን!' የሚል የልቅሶ ድምፅ በጽዮን ተሰምቶአል።
20ስለዚህ እናንተ ሴቶች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ ከአፉ ለሚወጣው ቃል ትኩረት ስጡ። ከዚያም ለሴቶች ልጆቻችሁም የልቅሶውን ዝማሬ አስተምሩ፣ ለእያንዳንዷም የጎረቤታችሁ ሴት የቀብሩን ሙሾ አስተምሩ።
21ሞት ወደ መስኮታችን መጥቷልና፤ ወደ ቤተ መንግሥቶቻችን ሄዷል። ሕፃናቱን ከውጪ፣ ወጣቶቹንም ከከተማይቱ አደባባይ ያጠፋል።
22'የሰውም ሬሳ በሜዳ ላይ እንደ ጕድፍ፣ ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል፣ ማንምም አይሰበስበውም።
23እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ጠቢብ በጥበቡ እንዲመካ አትፍቀዱ፣ ወይም ጦረኛ በኃይሉ አይመካ። ባለ ጠጋም በብልጥግናው እንዲመካ አትፍቀዱ።
24ሰው በየትኛውም ነገር የሚመካ ከሆነ፣ በዚህ ይሁን፣ ማስተዋል ያለውና የሚያውቀኝ በመሆኑ። የኪዳን ታማኝነት፣ ፍትሕንና ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፣ ይላል እግዚአብሔር።
25ተመልከቱ፣ በሰውነታቸው ብቻ የተገረዙትን እቀጣለሁ።
26ግብጽንና ይሁዳን፣ የአሞን ሕዝቦች የሆኑትን ኤዶምያስና ሞዓብንም፣ እንዲሁም በምድረ በዳም የተቀመጡትን ፀጉራቸውን የተላጩትን ሁሉ፣ ባለመገረዛቸው ምክንያት የምቀጣበት ዘመን እነሆ ይመጣል። እነዚህ ሁሉ ሕዝቦች ያልተገረዙ ናቸውና፣ ደግሞም የእስራኤል ልብ አልተገረዘምና" ይላል እግዚአብሔር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።