መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኤርሚያስ 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እናንተ የብንያም ሕዝቦች፣ ከኢየሩሳሌም በመሸሽ ደህንነትን አግኙ። በቴቁሔ መለከትን ንፉ። ታላቅ ጥፋት የሆነ ክፉ ነገር ከሰሜን እየመጣ ነውና በቤትሐካሬም ላይ ምልክትን አንሡ።
2የተዋበችውና ሰልካካዋን የጽዮንን ልጅ እደመስሳለሁ።
3እረኞችና መንጐቻቸው ወደ እርስዋ ይሄዳሉ፣ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፣ እያንዳንዱም እረኛ በገዛ እጁ መንጋውን ይጠብቃል።
4ነገሥታት "ለአማልክቶቻችሁ እንድትዋጉ ራሳችሁን አስገዙ። ተነሡ፣ በቀጥርም እናጥቃ። ቀኑ እየመሸ መሆኑ፣ የማታውም ጥላ እየረዘመ መሆኑ እጅግ መጥፎ ነው።
5ነገር ግን በሌሊትም እናጥቃ፣ አምባዎችዋንም እናፍርስ።
6የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ የከበባ አፈርን ደልድሉ፤ ይህች በግፍ የተሞላች ከተማ በመሆኗ ለማጥቃት ትክክለኛዋ ከተማ ነች።
7ጕድጓድ ውኃ ማፍለቊን እንደሚቀጥል፣ እንዲሁ ይህች ከተማ ክፋትን ማፍለቋን ትቀጥላለች። ዐመጽና ሥርዓተቢስነት በእርስዋ ዘንድ ይሰማል። መከራና መቅሠፍትም ሳይቋረጥ በፊቴ አለ።
8ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ከአንቺ እንዳልለይ፣ አንቺንም ባድማና ወና እንዳላደርግሽ፣ ተግሣጽን ተቀበዪ።"
9የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሰው ወይኑን እንደሚለቅም፣ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን በእርግጥ ይቃርሟቸዋል፤ በድጋሚ እጅህን ዘርግተህ ወይንን ከግንዱ እንደሚለቅም አድርግ።
10ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ፣ ለማንስ አስጠነቅቃለሁ? ተመልከቱ! ጆሮአቸው ያልተገረዘ ነው፤ በትኩረት ለመስማት አይችሉም! ተመልከቱ! የእግዚአብሔር ቃል ሊያቀናቸው መጥቶባቸዋል፣ ነገር ግን አይፈልጉትም።"
11ነገር ግን በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ። በውስጤ ይዤ ልታገሠው ደክሜአለሁ። እንዲህ አለኝ፣ "በጎዳና ሕፃናት ላይ፣ እንዲሁም በወጣቶችም ስብስብ ላይ አፍስሰው። እያንዳንዱ ባል ከሚስቱ ጋር እድሜ ጠገቡ ሽማግሌም ከጎበዙ ጋር ይወሰዳልና።
12ቤቶቻቸው እርሻዎቻቸውም ሚስቶቻቸውም በአንድነት ለሌሎች ይሆናሉ። በምድር የሚገኙ ነዋሪዎችን አጠቃለሁና ይላል እግዚአብሔር።
13ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ እያንዳንዳቸው በኃቅ ላልሆነ ትርፍ ስስታሞች ናቸው። ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ እያንዳንዳቸው በተንኰል ይመላለሳሉ።
14የሕዝቤንም ስብራት የሚፈውሱት ግን በጥቂቱ ነው፣ ሰላም ሳይኖር 'ሰላም ሰላም!' ይላሉ።
15ርኩስን ነገር ስለሠሩ አፍረዋልን? በጭራሽ አልፈሩም፣ ማንኛውንም እፍረት አላወቁም። ስለዚህ በምቀጣቸው ጊዜ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ። ይገለበጣሉ፣" ይላል እግዚአብሔር።
16እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በመንገድ ማቋረጫ ላይ ቁሙና ተመልከቱ፣ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ። 'መልካሚቱ መንገድ ወዴት ናት?' በሉና በእርስዋ ላይ ሄዳችሁ ለነፍሳችሁ ዕረፍትን አግኙ። ሕዝቡ ግን፣ 'አንሄድባትም' አሉ።
17እኔም የመለከቱን ድምፅ እንዲያደምጡ ጠባቂ ጉበኞችን ሾምሁላችሁ። እነርሱ ግን፣ 'አናደምጥም' አሉ።
18አሕዛብ ሆይ፥ አድምጡ! ተመልከቱ፣ በእነርሱ ላይ የሚደርስባቸውን ትመሰክራላችሁ።
19ምድር ሆይ፣ ስሚ! ተመልከቺ፣ የአሳባቸው ፍሬ የሆነ ጥፋትን በዚህ ህዝብ ላይ ላመጣ ነው። ለቃሌ ወይም ለህጌ ምንም ትኩረት አልሰጡም፣ ነገር ግን ከዚያ ይልቅ አጣጣሉት።"
20ከሳባ የሚቀርበው ዕጣን ለእኔ ምን ማለት ነው? ወይስ ከሩቅም አገር የሆነው ጣፋጭ ሽታ ምንድነው? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፣ እንዲሁም መስዋዕቶቻችሁን አልቀበለውም።
21ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ በዚህ ሕዝብ ፊት ዕንቅፋቶችን አደርጋለሁ። አባቶችና ልጆች በአንድነት ይሰናከሉባቸዋል። ነዋሪዎችና ጎረቤቶቻቸው ይጠፋሉ።
22እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ ሕዝብ ከሰሜን ምድር ይመጣል። ታላቅ ሕዝብም ከምድር ዳርቻ ይነሣል።
23ቀስትንና ጦርን ያነሣሉ። ጨካኞች ናቸው፣ ምሕረትንም የላቸውም። ድምፃቸው እንደ ባሕር ጩኸት ነው፣ በጽዮን ሴት ልጅ ላይ እንደሚዋጉ በፈረሶችም ላይ ይጋልባሉ።"
24ስለ እነርሱ ወሬውን ሰምተናል። እጃችን በጭንቀት ዝላለች። ምጥ ወላድን ሴት እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞናል።
25የጠላት ሰይፍና ሽብር ስለከበባችሁ ወደ ሜዳ አትውጡ፣ በመንገድም ላይ አትሂዱ።
26የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ፣ ማቅ ልበሺና ለብቸኛ ልጅ መቀበሪያ አፈር ውስጥ ተንከባለዪ። አጥፊው በድንገት ይመጣብናልና ለራስሽ መራራ የሆነ የቀብር ለቅሶን አድርጊ።
27"ኤርምያስ፣ መንገዳቸውን እንድትመረምርና እንድትፈትን በሕዝቤ መካከል ብረትን እንደሚፈትን አድርጌሃለሁ።
28እነርሱ ሁሉ ሌሎችን የሚወነጅሉ እጅግ ዐመፀኞች ናቸው። በብልሹነት የሚመላለሱ ናስና ብረት ናቸው።
29ወናፍ በሚያቃጥላቸው እሳት አናፋ፣ እርሳሱም በእሳቱ ቀለጠ። ክፋት ስላልተወገደ፣ የማጥራቱ ሥራ በመካከላቸው ይቀጥላል።
30እግዚአብሔር ጥሎአቸዋልና የተጣለ ብር ብለው ይጠሯቸዋል።"
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።