መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኤርሚያስ 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፤ በአደባባዮችዋም ፈልጉ። ከዚያም ተመልከቱ፣ ስለዚህም አስቡ፦ ፍትሕን የሚያደርገውን በታማኝነትም ለማድረግ የሚሞክረውንም ሰው ታገኙ እንደሆነ፣ ይቅር እላታለሁ።
2እነርሱም 'ሕያው እግዚአብሔርን!' ቢሉ የሚምሉት በሐሰት ነው።
3እግዚአብሔር ሆይ፣ ዓይንህ ታማኝነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፣ ነገር ግን አላመማቸውም። ሙሉ ለሙሉ አሸንፈሃቸዋል፣ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ። ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱ ዘንድ እንቢ አሉ።
4ስለዚህ እኔም "እነዚህ ድሆች ብቻ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው። የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ ሰነፎች ናቸው፤
5ወደ ጠቃሚዎቹ ሕዝቦች እሄዳለሁ የእግዚአብሔርን መልእክት እናገራቸዋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና። ነገር ግን እነርሱ በሙሉ ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፣ ለእግዚአብሔር ያሰራቸውንም ሰንሰለቶች ቈርጠዋል።
6ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፣ የክዳታቸውም ብዛት አይቆጠርምና አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፣ የበረሀም ተኵላ ያጠፋቸዋል፣ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፣ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።
7እነዚህን ሰዎች ይቅር የምላቸው ለምንድነው? ልጆችሽ ትተውኛል አማልክትም ባልሆኑትም ምለዋል። ሞልቼ መገብኳቸው፣ እነርሱ ግን አመነዘሩ የምንዝርና ቤትን ምልክቶችንም ወሰዱ።
8በትኩሳት እንዳሉ ፈረሶች ሆኑ፤ ወዳጅነት ፈልገው ተንከላወሱ። እያንዳንዱ ሰው ወደባልንጀሮቻቸው ሚስቶች አሽካኩ።
9ስለዚህ ልቀጣ አይገባኝምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?
10ወደ ወይን ከፍታዋ ወጥታችሁ አፍርሱ። ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፏቸው። ወይኖቻቸውን ቊረጡ፣ እነዚህ ወይኖች ከእግዚአብሔር አልመጡምና።
11የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ ፈጽሞ ከድተውኛልና ይላል እግዚአብሔር።
12እነርሱም ከድተውኛል። 'እርሱ እውነተኛ አይደለም። ክፉ ነገርም አይመጣብንም፣ ሰይፍንና ራብንም አናይም' አሉ።
13ነብያትም የነፋስን ያህል ጥቅም የለሽ ሆነዋል የእግዚአብሔርንም ቃል ለእኛ የሚነግረን የለም። ዛቻቸው በራሳቸው ላይ ይምጣባቸው።
14ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል "በዚህ ቃል ተናግራችኋልና ተመልከት፣ በአፍህ ውስጥ ቃሌን አኖራለሁ። እንደ እሳት ይሆናል፣ ይህም ሕዝብ እንደ እንጨት ይሆናል! እሳቱም ይበላቸዋል።
15ተመልከቱ! የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃያል ጥንታዊ ሕዝብ ነው! ቋንቋቸውንም የማታውቋቸው፣ የሚናገሩትንም የማታስተውሉት ሕዝብ ነው።
16የፍላጻቸውም ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው። ሁሉም ኃያላን ናቸው።
17መከሮቻችሁንና እንጀራችሁን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም ይበሏቸዋል፤ በጎችንና ላሞቻችሁንም ይበላሉ፤ ወይናችሁንና በለሶቻችሁንም ይበላሉ። የምትታመኗቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደበድባሉ።
18ነገር ግን በዚያ ዘመን እንኳን ይላል እግዚአብሔር፣ ፈጽሜ ላጠፋችሁ አላስብም።
19እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ እስራኤል እና ይሁዳ፣ 'አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለምን አደረገብን?' ስትሉ፣ አንተ ኤርምያስ ያን ጊዜ፣ 'እግዚአብሔርን እንደተዋችሁ እና በምድራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ፣ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ አገር ለሌሎች ሰዎች በባርነት ትገዛላችሁ' ትላቸዋለህ።
20ይህን ለያዕቆብ ቤት አውሩ፣ በይሁዳም ይሰማ።
21ይህን ስሙ፣ እናንተ ሰነፎች! ጣዖታት ፈቃድ የላቸውምና፤ ዐይን አለባቸው፣ ነገር ግን ሊያዩ አይችሉም። ጆሮዎችም አሉባቸው፣ ነገር ግን አይሰሙም።
22እኔን አትፈሩኝምን? በፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ የአሸዋን ድንበር እንዳይተላለፈው በማይቋረጥ ትእዛዝ በባሕሩ ላይ አድርጌአለሁ። የባህሩ ነውጥ ቢጮኽም አያቋርጠውም።
23ነገር ግን ይህ ሕዝብ ግን ዐመፀኛ ልብ አለው። በዐመፅ ሸፍቶ ሄዷል።
24በልባቸውም፣ 'የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በትክክለኛው ጊዜ የሚሰጠውን፣ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ አላሉም።
25በደላችሁ እነዚህ እንዳይሆኑ አስቀርታለች። ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ወደ እናንተ እንዳይመጣ አስቆመ።
26በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል። አንድ ሰው ወፎችን ለመያዝ ሲያደባ እንደሚመለከቱ፣ ወጥመድን ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ።
27ዋሻ ወፎችን እንደሚሞላ፣ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች። እንዲሁም ተልቀዋል፣ ባለ ጠጎችም ሆነዋል።
28ወፍረዋል፣ በደህንነታቸውም ያብረቀርቃሉ። ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል። ለሰዎች፣ ወይም ለወላጅ አልባዎች ነገር አልተምዋገቱላቸውም። ለችግረኞች ፍትሕን ባያደርጉም እንኳን በልጽገዋል።
29ስለእነዚህ ነገሮች አልቀጣምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ ለራሴ አልበቀልምን?
30በምድር ላይ የምታስደንቅና የምታስደነግጥ ነገር ሆናለች፤
31ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፣ ካህናትም በገዛ ኃይላቸው ይገዛሉ። ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፣ ነገር ግን በፍጻሜው ምን ይፈጠራል?
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።