መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኤርሚያስ 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እስራኤል ሆይ፣ ብትመለሺ፣ የምትመለሺው ወደ እኔ ይሁን፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ከፊቴ ርኩሰትሽን ብታስወግጂ፣ በድጋሚም ከእኔ ባትርቂ
2'ሕያው እግዚአብሔርን!' ብለሽ በእውነትና በፍትሕ፣ በጽድቅም ብትምይ፥ አሕዛብ በረከቴን ይጠይቃሉ፣ እኔንም ያመሰግኑኛል።
3ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ጥጋቱን እርሻ እረሱ፣ በእሾህም ላይ አትዝሩ።
4እናንተም የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፣ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቊጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።
5ይሁዳ ውስጥ ተናገሩ፣ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩ። "በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ" በሉ፤ ጮኻችሁም "ሁላችሁ ተሰብሰቡ። ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ" በሉ።
6ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ሰንደቅ ዓላማን አንሡ፤ ሽሹ፥ አትዘግዩ።
7አንበሳ ከጥቅጥቅ ዱር እየወጣ ነው፣ አሕዛብንም የሚያጠፋ እየወጣ ነው። ምድርሽን ለማሸበር፣ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ለማድረግ ከስፍራው ወጥቶአል።
8ከዚህ የተነሣ፣ ራስሽን በማቅ ልብስ ሸፍኚ፣ ሙሾ አውጪ፣ አልቅሺም። የእግዚአብሔር ጽኑ ቊጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰምና።
9በዚያም ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይሞታል። ካህናቱም ይደነቃሉ ነቢያቱም ይደነግጣሉ።
10እኔም "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ፥ 'ሰላም ይሆንላችኋል' በማለት ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን በእርግጥም ፈጽመህ አታልለሃል። ሆኖም 'ሰይፉ እስከ ነፍስ ድረስ ያጠቃል።"
11በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም፣"የሚያቃጥል ነፈሳስ በምድረበዳ ካሉት ወና ኮረብቶች ወደ ሕዝቤ ሴት ልጅ ይመጣል። እነርሱን አያበጥርም ወይም አያጠራም።
12ከዚያም ይልቅ እጅግ ብርቱ የሆነ ነፋስ በትእዛዜ ይመጣል፣ ደግሞም እኔ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።
13ተመልከቱ እንደ ደመና ያጠቃል፣ ሠረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው። ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ጠፍተናልና ወዮልን!
14ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ትድኚ ዘንድ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። እንዴት ኃጢአት እንደምትሠሪ ክፉ አሳብ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው?
15የተናጋሪ ድምፅ ከዳን ይናገራል። የሚመጣውም ጥፋት ከኤፍሬምም ተራሮች ይሰማል።
16አሕዛብ ይህንን እንዲያስቡ አድርጉ፦ ተመልከቱ፣ ወራሪዎች በይሁዳ ከተሞች ላይ የጦርነት ጩኸት ለመጮኽ ከሩቅ ምድር እየመጡ ነው ብላችሁ አውሩ።
17በእኔ ላይ ዓመፀኛ ሆናለችና የለማ እርሻን ከብበው እንደሚጠብቊ ይሆናሉ ይላል እግዚአብሔር።
18ባሕርይሽና ሥራሽ ይህን አድርጎብሻል። ይህ ቅጣትሽ ይሆናል። እንዴት አስጨናቂ ይሆናል! የገዛ ልብሽም ይመታል።
19ልቤ! ልቤ! በልቤ ተጨንቄያለሁ። ልቤ በውስጤ ታውኮብኛል። የመለከትን ድምፅና የጦርነት ማንቂያን ሰምቻለሁና ዝም ልል አልችልም።
20በጥፋት ላይ ጥፋት ተጠርቶአል፣ መላዋ ምድርም ተበዝብዛለች። በድንገትም ድንኳኔንና መጋረጃዬን አጠፉ።
21መስፈርቱን የምመለከተው እስከመቼ ነው? የመለከቱንስ ድምፅ እሰማ ይሆን?
22ሕዝቤ ተሞኝተዋልና አላወቁኝም። ሰነፍ ሕዝብ ናቸው፣ ማስተዋልም የላቸውም። ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፣ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።
23ምድሪቱን አየሁ፣ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ ለሰማያትም ብርሃንም አልነበረባቸውም።
24ተራሮችን አየሁ። እነሆም፣ ይንቀጠቀጡ ነበር፣ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ።
25አየሁ። እነሆ፣ ሰው አልነበረም፣ የሰማይም ወፎች ሁሉ ሸሽተው ነበር።
26ተመለከትሁ። እነሆ፣ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፣ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቊጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር።
27እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል "ምድር ሁሉ ትጠፋለች፣ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋቸውም።
28ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፣ ከላይ ያለው ሰማይ ይጠጨልማል። ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፤ አልጸጸትም ከመፈጸምም አልመለስም።
29ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ጫጫታ የተነሣ እያንዳንዱ ከተማ ሁሉ ይሸሻሉ፤ ወደ ጫካም ይገባሉ። እያንዳንዱ ከተማ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ። ከተሞቹ ይተዋሉ፣ የሚኖርባቸው ሰው አይኖርምና።
30አንቺም ባድማ ሆንሽ፥ ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም አጌጥሽ፣ ዓይንሽንም ተኳልሽ፣ የሚመኙሽ ወንዶች ገፉሽ። ይልቊን፣ ነፍስሽን ይሹአታል።
31ስለዚህ የምጥ፣ የበኩር ልጅ እንደሚወለድበት ያለ የጭንቅ ድምጽ፣ የጽዮን ሴት ልጅን ድምጽ ሰምቻለሁ። ለመተንፈስ ትታገላለች። እጆቿንም ትዘረጋለች፣ ከገዳዮቹ የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና 'ወዮልኝ!' አለች።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።