1ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ይህ ቃል ወደ እርሱ የመጣው ፈርዖን ጋዛን ሳይመታ በፊት ነው።
2"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ውኃ ከሰሜን ይነሣል። እነርሱም እንደሚያጥለቀልቅ ፈሳሽ ይሆናሉ! ከዚያም በምድሪቱና በመላዋ ሁሉ፣ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ይጐርፋሉ! ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ለእርዳታ ይጮኻል፣ በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።
3ከኃይለኞች ፈረሶች ከኮቴያቸው መጠብጠብ ድምፅ፣ ከሰረገሎቹና ከጎማዎቻቸውም መሸከርከር ሁከት የተነሣ፣ አባቶች በገዛ ራሳቸው ድካም ምክንያት ልጆቻቸውን አይረዱም።
4ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ያጠፋ ዘንድ የቀሩትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና የሚቆርጥ ቀን ስለሚመጣ ነው። እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንና የከፍቶርን ደሴት ቅሬታ ያጠፋልና።
5ራሰ ቡሀነት በጋዛ ላይ መጥቶአል። አስቀሎናን በተመለከተ፣ በሸለቋቸው የተተዉት ሕዝብ ዝም እንዲሉ ይደረጋሉ። እስከ መቼ ድረስ በለቅሶ ራሳችሁን ትነጫላችሁ?
6ወዮ፣ የእግዚአብሔር ሰይፍ! ዝም እስከምትል ምን ያክል ትቆያለህ? ወደ ሰገባህ ተመለስ! ቊም ደግሞም ጸጥ በል።
7እግዚአብሔር አዝዞሃልና እንዴት ዝም ልትል ትችላለህ። በአስቀሎናና በባሕር ዳር ላይ ጥቃት እንድትፈጽም አዘጋጅቶሃልና።"