1ኤርምያስ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ የነገረው ቃል ይህ ነበር። ይህም የሆነው በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት ኤርምያስ እየነገረው በመጽሐፍ በጻፋቸው ጊዜ ነበር፤ እርሱም እንዲህ አለ፣
2"ባሮክ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል፦
3አንተ፣ 'እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ኀዘንን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ። በልቅሶዬ ጩኸት ደክሜአለሁ፤ ዕረፍትንም አላገኘሁም' ብለሃል።
4ልትለው የሚገባህ ይህንን ነው፦ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ የሠራሁትን፣ አሁን እያፈረስኩ ነው። የተከልሁትንም፣ እየነቀልሁ ነው። ይኽም በምድር ሁሉ ላይ እውነት ነው።
5ነገር ግን ለራስህ ታላቅ ነገር ተስፋ ታደርጋለህን? ያንን ተስፋ አታድርግ። በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ክፉ ነገርን እንደማመጣ ትመለከታለህና አትፈልገው፣ ይላል እግዚአብሔር። ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።"