መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኤርሚያስ 43

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኤርምያስ አምላካቸው እግዚአብሔር ለእነርሱ የላከውን ይህንን የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ፣ለሕዝቡ ሁሉ ተናግሮ ጨረሰ።
2የሆሻያ ልጅ ዓዛርያስ፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ ትዕቢተኞችም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን፣ "ሐሰትን እየተናገርክ ነህ። አምላካችን እግዚአብሔር፣ 'በዚያ ትቀመጡ ዘንድ ወደ ግብጽ አትግቡ ብሎ አልላከህም፤'
3ነገር ግን ከለዳውያን እንዲገድሉን ወደ ባቢሎንም እንዲማርኩን በእጃቸው አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ የኔርያ ልጅ ባሮክ በላያችን ላይ አነሣሥቶሃል" አሉት።
4ስለዚህ የቃሬያ ልጅ ዮሐናን፣ የጦር ሠራዊቱ አለቆች ሁሉ፣ ሕዝቡም ሁሉ በይሁዳ ምድር ይኖሩ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።
5የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመኖር ከተሰደዱባቸው ከአሕዛብ ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታ ሁሉ ወሰዱ።
6እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆችን፣ የንጉሡንም ሴቶች ልጆች፣ የዘበኞቹንም አለቃ ናቡዘረዳን፣ ከሳፋን ልጅ፣ ከአኪቃም ልጅ ከጎዶልያስ ጋር የተዋቸውን ሰዎች ሁሉ፣ ነቢዩንም ኤርምያስን የኔርያንም ልጅ ባሮክን ወሰዱ።
7የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልሰሙ ወደ ግብጽ ምድር ሄዱ፣ እስከ ጣፍናስ ድረስ መጡ።
8ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል በጣፍናስ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
9"ታላላቆችን ድንጋዮች በእጅህ ውሰድ፣ የይሁዳም ሰዎች እያዩ በጣፍናስ ባለው በፈርዖን የጡብ ቤት ደጅ መግቢያ ሸሽጋቸው።"
10ከዚያም እንዲህ በላቸው፣ "የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አገልጋዬ ለማድረግ መልእክተኛ እልክበታለሁ። ዙፋኑንም አንተ፣ ኤርምያስ በሸሸግሃቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ። ናቡከደነፆር ማለፊያ ድንኳኑን በላያቸው ይዘረጋል።
11መጥቶም የግብጽን ምድር ያጠቃል። ለሞት የተመደበውን ለሞት ይሰጣል። ለምርኮም የተመደበው ለምርኮ ይወሰዳል። ለሰይፍ የተመደበው ለሰይፍ ይሰጣል።
12ከዚያም፣ በግብጽ አማልክት ቤቶች ላይ እሳትን አነድዳለሁ። ናቡከደነፆር ያቃጥላቸዋል ወይም ይማርካቸዋል። እረኞች ከደበሏቸው ተባይን እንደሚያራግፉ፣ እንዲሁ የግብጽን አገር ያጸዳል። ከዚያም ስፍራ በድል ይወጣል።
13በግብጽም ምድር ያለውን የሄልዮቱን ከተማ ሐውልቶች ይሰብራል። የግብጽንም አማልክት ቤቶች በእሳት ያቃጥላል።"
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።