መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኤርሚያስ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በሰው ዘንድ፣ 'ሰው ሚስቱን በፍቺ ቢያባርራት፣ ከእርሱም ሄዳ የሌላ ሰው ሚስት ትሆናለች። በድጋሚ ወደ እርሷ ሊመለስ ይገባዋልን? እርሷ ፈጽሞ የረከሰች አይደለችምን?' ይባላል። ያቺ ሴት ማለት ይህች ምድር ናት! አንቺ እንደ ሴተኛ አዳሪ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፣ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር።
2ዓይንሽን ወደ ተራቆቱት ኮረብቶች አንሺና ተመልከቺ! ያልተነወርሽበት ስፍራ ወዴት አለ? ዘላን በምድረ በዳ እንደሚቀመጠው፣ አንቺ በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ አፍቃሪዎችሽን ትጠብቂያቸው ነበር። በዘማዊነትሽና በኃጢአትሽ ምድሪቱን አረከስሽ።
3ስለዚህ የጸደይ ዝናብ ተከለከለ፣ የኋለኛውም ዝናብ አልመጣም። ነገር ግን እንደ ዘማዊት ሴት ፊት፣ ፊትሽ የእብሪተኛ ነበር። ልታፍሪም እንቢ ብለሻል።
4ከእንግዲህ ወዲህ 'አባቴ! የወጣትነቴ የቅርብ ወዳጅ ነህ።' ብለሽ ወደ እኔ አልጮኽሽልኝምን?
5እስከ ለዘላለም ትቆጣለህን? ቊጣህንስ እስከ ፍጻሜ ድረስ ትጠብቀዋለህን?' ብለሽ ተናገርሽ። ተመልከቺ! ክፋትን እንደምትፈጽሚ ተናገርሽ፣ አደረግሸውም። ስለዚህ ማድረግሽን ቀጥይ!"
6እግዚአብሔርም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ "እስራኤል እኔን መክዳቷን ታያለህ? ከፍ ወዳለው ተራራ ሁሉ፣ ወደለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፣ በዚያም እንደ ዘማዊት ሴት ሆነች።
7'ይህንም ሁሉ ካደረገች በኋላ፣ ወደ እኔ ትመለሳለች' ብዬ ነበር፤ ነገር ግን አልተመለሰችም። ከዚያም እምነት የለሿ እኅቷ ይሁዳ እርሷ ያደረገችውን አየች።
8ስለዚህ፣ ለእነዚህ ምክንያቶች ሁሉ ማመንዘሯን አየሁ። ከዳተኛይቱ እስራኤል! ፈትቼያት አባርሬያታለሁ፣ ደግሞም የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ። አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን አልፈራችም፣ እርስዋም ደግሞ ሄዳ ዝሙትን ፈጸመች።
9በዝሙትዋ ምድሪቱ መርከሷ ምንም አልመሰላትም፣ ስለዚህ ከድንጋይና ከግንድ ጣዖታትን አደረጉ።
10ከዚያም ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ፣ እምነት-የለሿ ይሁዳ በውሸት እንጂ በፍጹም ልብዋ ወደ እኔ አልተመለሰችም!"-ይላል እግዚአብሔር።
11ከዚያም እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ከእምነት-የለሿ ይሁዳ ይልቅ እምነት-የለሿ እስራኤል ጸደቀች!
12ሂድና ይህን ቃል ለሰሜን ተናገር። 'እምነት የለሿ እስራኤል ሆይ፥ ተመለሽ! ይላል እግዚአብሔር፤ ለሁልጊዜ አልቈጣብሽምና። እኔ ታማኝ ስለሆንኩ - ለዘላለም እንደተቆጣሁ አልቆይም ይላል እግዚአብሔር።
13በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ቃሌንም እንዳልሰማሽ ኃጢአትሽን ዕወቂ ይላል እግዚአብሔር።
14አግብቻችኋለሁና እምነት-የለሽ የሆናችሁት ሕዝቦች፣ ተመለሱ! ይላል እግዚአብሔር፤ አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ! ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ!
15እንደ ልቤም የሆኑ እረኞችን እሰጣችኋለሁ፣ እነርሱም በዕውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል።
16በእነዚያ ቀናት ትበዛላችሁ፣ በምድሪቱም ላይ ታፈራላችሁ ይላል እግዚአብሔር። "የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት!" ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይናገሩም። ከእንግዲህ አያስቡትምና፣ ወይም አያስተውሉትምና ይህ ጉዳይ ከእንግዲህ በልባቸው አይመጣም። ከእንግዲህ ወዲህም ይህ ንግግር አይኖርም።'
17በዚያም ዘመን ስለ ኢየሩሳሌም 'ይህች የእግዚአብሔር ዙፋን ናት' ብለው ይናገራሉ፣ ደግሞም ሌሎች አሕዛብ ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ኢየሩሳሌም ላይ ይሰበሰባሉ። ከእንግዲህም ወዲህ በእልከኛ ልባቸው አይሄዱም።
18በእነዚያም ቀናት፣ የይሁዳ ቤት ከእስራኤል ቤት ጋር ይሄዳል። በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።
19እኔ ግን 'እንደ ወንድ ልጄ ላከብርሽና በሌሎች አሕዛብ ካለው ይልቅ የበለጠ ውብ የሆነውን አስደሳቹን ምድር ልሰጥሽ እንዴት ፈለግሁ!' ብዬ ነበር። "አባቴ" ብለሽ ትጠሪኛለሽ። እኔንም ከመከተል አትመለሽም' ብዬ ነበር።
20ነገር ግን ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች ሴት፣ እንዲሁ የእስራኤል ቤት የሆናችሁት ከዳችሁኝ ይላል እግዚአብሔር።
21"የእስራኤል ልጆች መንገዳቸውን ቀይረዋልና፣ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተውኛልና በወና ኮረብቶች ላይ የልመናቸውና ልቅሶአቸው ድምፅ ተሰማ።
22ከዳተኞች ሕዝቦች ሆይ ተመለሱ! ከዳተኛነታችሁንም እፈውሳለሁ!" እነሆ! አንተ አምላካችን እግዚአብሔር ነህና ወደ አንተ እንመጣለን።
23የኮረብቶችና የብዙ ተራሮች ሐሰት ብቻ መጥቷል። በእርግጥም የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ነው።
24ይሁን እንጂ አሳፋሪ ጣዖታት ለበጎቻቸውና ላሞቻቸው፣ ለወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው አባቶቻችን የሠሩትን በልተውባቸዋል።
25በእፍረት እንጋደም። በአምላካችን እግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተናልና እፍረታችን ይሸፍነን። ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፣ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና!"
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።