መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኤርሚያስ 34

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። ይህ ቃል የመጣው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ፣ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና ከተሞችዋን ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ ነበር።
2'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሂድ ለይሁዳም ንጉሥ ለሴዴቅያስ ተናገር እንዲህም በለው፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ይህችን ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። በእሳትም ያቃጥላታል።
3አንተም በእርግጥ ትያዛለህ፣ በእጁም ተላልፈህ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም። ዐይንህም የባቢሎንን ንጉሥ ዐይን ታያለች፤ ወደ ባቢሎን ስትሄድ፣ እርሱ ከአንተ ጋር አፍ ለአፍ ይነጋገራል።'
4የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ! ስለ አንተ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'በሰይፍ አትሞትም።
5በሰላም ትሞታለህ። እንደ አባቶችህ የቀብር መቃጠል፣ ከአንተ በፊት እንደነበሩት ነገሥታት፣ እንዲሁ አካልህን ያቃጥላሉና። "ወየው፣ ጌታ ሆይ!" እያሉ ያለቅሱልሃል። አሁን እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር።"
6ነቢዩ ኤርምያስ እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ነገረው።
7የባቢሎንም ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳን ከተሞች ሁሉ፦ ለኪሶንና ዓዜቃን ወጋ። እነዚህ የይሁዳ ከተሞች የተመሸጉ ከተሞች ሆነው ቀሩ።
8ንጉሡ ሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ከነበሩ ሕዝብ ሁሉ ጋር ነፃነትን ለማወጅ ስምምነት ካደረገ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
9እያንዳንዱ ሰው እስራኤላዊ የሆነውን ወንድ ባርያውንና ሴት ባርያውን ነፃነት ሊለቅ ይገባል። ማንም ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በይሁዳ ውስጥ መሰል እስራኤላዊን ባርያ ሊያደርግ አይገባም።
10ስለዚህም ስምምነቱን የተቀላቀሉት መሪዎች ሁሉ እና ሕዝቡ ታዘዙ። እያንዳንዱ ሰው ወንድ እና ሴት ባርያዎቻቸውን ከእንግዲህ ወዲህ ባርያ ላያደርጓቸው ነፃ አደረጓቸው። እነርሱም ሰሙ፣ ሰደዷቸውም።
11ነገር ግን ከዚህ በኋላ አሳባቸውን ቀየሩ። ነፃነት የለቀቋቸውን ባርያዎቻቸውን መልሰው አመጡ። በድጋሚ ባርያዎች እንዲሆኑ አስገደዷቸው።
12ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
13"የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'አባቶቻችሁን ከባርነት ቤት ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከእነርሱ ጋር እንዲህ ብዬ ቃል ኪዳን አደረግሁ።
14"ሰባት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፣ ራሱን የሸጠላችሁን፣ ስድስትም ዓመት የተገዛላችሁን ዕብራዊ ወንድማችሁን እያንዳንዳችሁ ነፃነት ልታወጡት ይገባል። ነፃ አድርጋችሁ ስደዱት።" ነገር ግን አባቶቻችሁ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።
15እናንተም ዛሬ ተመልሳችሁ ሰው ሁሉ ባልንጀራውን አርነት ለማውጣት ዐዋጅ በመንገር ለዐይኔ ትክክል የሆነውን ነገር አድርጋችሁ ነበር። በስሜም በሚጠራበት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድርጋችሁ ነበር።
16ነገር ግን ያን ጊዜ ተመልሳችሁ ስሜን አስነቀፋችሁ፤ እያንዳንዳችሁም በፈቃዳቸው እንዲሄዱ ነፃነት ያወጣችኋቸውን ወንድና ሴት ባርያዎቻችሁን አስመለሳችሁ። በድጋሚ ወንዶችና ሴቶች ባርያዎች እንዲሆኑላችሁ አስገደዳችኋቸው።'
17ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'እናንተ ራሳችሁ አልሰማችሁኝም። እያንዳንዳችሁ፣ ለወንድሞቻችሁና ለመሰል እስራኤላውያን ነፃነትን ልታውጁ በተገባ ነበር። ስለዚህ ተመልከቱ! እኔ ለሰይፍ፣ ለመቅሰፍት፣ ለራብም የነፃነት ዐዋጅ እናገርባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል አስደንጋጭ ነገር አደርጋችኋለሁ።
18ከዚያም ቃል ኪዳኔን የተላለፉትን ሰዎች፣ እንቦሳውንም ቈርጠው በቍራጩ መካከል ባለፉ ጊዜ በፊቴ ያደረጉትን የቃል ኪዳንን ቃል ያልፈጸሙትን እቀጣለሁ፤
19ከዚያም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን አለቆች ጃንደረቦችን ካህናትንም፣ በእንቦሳም ቍራጭ መካከል ያለፉትን የአገሩን ሕዝብ ሁሉ።
20ለጠላቶቻቸው እጅ፣ ሕይወታቸውንም ለሚሹአት ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።
21የይሁዳንም ንጉሥ ሴዴቅያስንና አለቆቹን ለጠላቶቻቸው እጅ፣ ሕይወታቸውንም ለሚሹአት እጅ፣ ከእናንተም ለተመለሱት ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ።
22ተመልከቱ፣ ትእዛዝ እሰጣለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ጦርነትን እንዲከፍቱባትና እንዲወስዷት፣ እንዲያቃጥሏትም ወደዚህች ከተማ እመልሳቸዋለሁ። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።"
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።