1በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት፣ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
2ይህንም ቃል ነቢዩ ኤርምያስ ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ።
3"ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ ልጅ ከኢዮስያስ አሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሀያ ሦስቱ ዓመታት፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ ሲመጣ ነበር። እነግራችሁም ነበር። እነግራችሁ ነበር፣ ነገር ግን አልሰማችሁም።
4እግዚአብሔርም ባርያዎቹን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ ላከ። እነርሱም ለመውጣት ጉጉዎች ነበሩ፣ ነገር ግን እናንተ አላደመጣችሁም ትኩረትም አልሰጣችሁትም።
5እነዚህ ነብያት፣ 'እያንዳንዱ ሰው ከክፉ መንገዱና ከሥራችሁ ብልሹነት ተመለሱና እግዚአብሔር ከጥንት ጊዜያት ጀምሮ ቋሚ ስጦታ አድርጎ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣችሁ ምድር ተቀመጡ።
6ታመልኩአቸው፣ ትሰግዱላቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፣ ክፉም እንዳያደርግባችሁ በእጃችሁ ሥራ አታስቈጡኝ አለ።
7ለእናንተ ጕዳት እንዲሆን በእጃችሁ ሥራ ታስቈጡኝ ዘንድ አልሰማችሁኝም፣ ይላል እግዚአብሔር።
8ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ቃሌን አልሰማችሁምና፣
9ተመልከቱ፣ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባርያዬ ከሆነው ከባቢሎን ንጉሥ ናብከደነዖር ጋር ለመሰብሰብ ትእዛዝን እልካለሁ፤ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፣ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ። ለማጥፋትም እለያቸዋለሁ። ለመጨነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
10ከእነርሱም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ፣ የወፍጮንም ድምፅ የመብራትንም ብርሃን አጠፋለሁ።
11ከዚያም ይህች ምድር ሁሉ ባድማና መደነቂያ ትሆናለች፣ ከዚያም እነዚህ አሕዛብ ለባቢሎን ንጉሥ ሰባ ዓመት ይገዛሉ።
12ሰባው ዓመትም የሚፈጸምበት ጊዜ ይመጣል፣ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ፣ የከለዳውያንን ምድር ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፣ የማያበቃ ባድማ አደርጋታለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
13በዚያችም ምድር ላይ የተናገርሁትን ቃሌን ሁሉ፣ እንዲሁም፣ ኤርምያስ በአሕዛብ ሁሉ ላይ የተነበየውን በዚህች መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ በዚያች ምድር አመጣለሁ።
14ብዙ ሌሎች አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት ከእነዚህ ሕዝቦች ውስጥ ባርያዎችን ያደርጋሉ። እኔም ስለ አደራረጋቸውና ስለ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።"
15የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፣ "የዚህን ቍጣ የወይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፣ አንተን ለምሰድድባቸው አሕዛብ ሁሉ አጠጣቸው።
16ከምሰድድባቸውም ሰይፍ የተነሣ ይጠጣሉ፣ ይሰናከላሉ፣ በእብደት ይለፈልፋሉ።
17ስለዚህ ጸዋውን ከእግዚአብሔር እጅ ወሰድሁ፣ ከዚያም እግዚአብሔርም እኔን ለላከባቸው አሕዛብ ሁሉ አጠጣኋቸው።
18በዚህ ዛሬ እንደሆኑት ሁሉ ባድማና መደነቂያ፣ ማፍዋጫም፣ እርግማንም አደርጋቸው ዘንድ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች፣ ነገሥታትዋንም፣ አለቆችዋንም አጠጣኋቸው።
19ሌሎች ሕዝቦችም እንዲሁ ሊጠጡት ይገባል፦ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንና ባርያዎቹ፤ አለቆቹና ሕዝቦቹ ሁሉ፤
20የተደባለቀ ቅርስ ሕዝቦች ሁሉ፣ የዖፅ ምድር ነገሥታት ሁሉ፣ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፣ አስቀሎና፣ ጋዛ፣ አቃሮን የአዞጦን ቅሬታ ሁሉ፤
21ኤዶምያስ፣ ሞዓብ፣ እና የአሞንም ሕዝቦች፤
22የጢሮስና ሲዶና ነገሥታ፣ በባህሩ ማዶ ያለች የደሴት ነገሥታትም፣
23ድዳን፣ ቴማን፣ ቡዝን፣ በራሳቸው ጎንና ጎን ጠጕራቸውን የሚቈርጡትን ሁሉ።
24እነዚህም ሕዝቦች እንዲሁ ሊጠጡት ይገባል፦ የዓረብ ነገሥታት ሁሉ፣ በምድረ በዳ የሚኖሩት የድብልቅ ቅርስ ሕዝብ ነገሥታት ሁሉ፣
25የዘምሪ ነገሥታት ሁሉ፣ የኤላም ነገሥታት ሁሉ፣ የሜዶን ነገሥታት ሁሉ፤
26የቀረቡና የራቁ፣ አንዱ ከሌላው ጋር ያሉ የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ፣ በምድር ገጽ ላይ ያሉ የዓለም መንግሥታት ሁሉ አጠጣኋቸው። በመጨረሻም፣ የባቢሎን ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል።
27"'የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምሰድደው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፣ ስከሩ፣ አስታውኩ፣ ውደቁ፣ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡ' በላቸው፤ አለኝ።
28እንዲጠጡ ጽዋውን ከእጅህ ለመቀበል እንቢ ቢሉ፣ 'የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእርግጥ ትጠጡታላችሁ፤ በላቸው።
29ተመልከቱ፣ ስሜ በተጠራባት ከተማ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ፣ እናንተ ራሳችሁ ያልተቀጣችሁ ትሆናላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና ከቅጣት ነፃ አትሆኑም፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።'
30ስለዚህ፣ አንተ ራስህ፣ ኤርምያስ እነዚህን ቃሎች ሁሉ ትተነብይባቸዋለህ፣ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ 'እግዚአብሔር ከበላይ ሆኖ ይጮኻል፣ ከቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል። በማደሪያው ላይ እጅግ ይጮኻል፣ ወይንን ሲሚጠምቁ እንደሚዘምሩት በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል።
31እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል። ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር በፍትህ ይፋረዳል። ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።'
32የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ጥፋት ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ይወጣል፣ ደግሞም ጽኑም ዐውሎ ነፍስ ከሩቅ የምድር ዳርቻ ይነሣል።
33ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ግዳዩች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበዛሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይሰበሰቡም፣ ወይም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ።
34እረኞች አልቅሱ፣ ለእርዳታም ጩኹ! በመንጋው ውስጥ አውራ የሆናችሁት ሕዝቦች በመሬት ላይ ተንከባለሉ። ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ መጥቷልና። እንደ ተመረጡ በጎች ትወድቃላችሁ።
35ወደእረኞች ለመሸሸግ ማምለጥ ይቀራል።
36እግዚአብሔር ማሰማርያቸውን አጥፍቶአልና የእረኞች ጩኸት ድምፅ፣ የመንጋ አውራዎችም ልቅሶ ሆኖአል።
37ከእግዚአብሔር ጽኑ ቊጣ የተነሣ የሰላም ማሰማሪያ ይፈርሳል።
38እንደ ታዳጊ አንበሳ መደቡን ለቅቆአል፣ ከአስጨናቂውም ሰይፍና ከጽኑ ቍጣው የተነሣ ምድራቸው አስፈሪ ሆናለችና።"