መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኤርሚያስ 24

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር አንድ ነገር አሳየኝ። እነሆ፣ በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት ሁለት ቅርጫት በለስ ተቀምጠው ነበር። (ይህ ራእይ የታየው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፣ የይሁዳንም አለቆች፣ ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችን ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው በኋላ ነበር።)
2በአንደኛው ቅርጫት አስቀድሞ እንደበሰለ በለስ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረበት፤ ነገር ግን በሁለተኛው ቅርጫት ውስጥ ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ በለስ ነበረበት።
3እግዚአብሔርም፣ "ኤርምያስ ሆይ፣ ምንታያለህ?" አለኝ። እኔም፣ "በለስን። እጅግ መልካም የሆነ በለስ፣ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ የሆነ በለስ አያለሁ።" አልሁ።
4የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
5"የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፣ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድሁትን የይሁዳን ምርኮ ለጥቅማቸው እመለከተዋለሁ።
6ዓይኔንም ለመልካም በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፣ ወደዚህችም ምድር እመልሳቸዋለሁ። እገነባቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም። እተክላቸዋለሁ፣ እንጂ አልነቅላቸውም።
7ከዚያም፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ እንዲመለሱ፣ ሕዝብ ይሆኑኛል፣ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
8ነገር ግን ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉው በለስ፣ እንዲሁ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን አለቆቹንም በዚህችም አገር የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቅሬታ በግብጽም አገር የሚቀመጡትን እጥላቸዋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
9በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ፣ ለማላገጫና ለእርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
10ለእነርሱና ለአባቶቻቸውም ከሰጠኋቸው ምድር እስኪጠፉ ድረስ በመካከላቸው ሰይፍንና ራብን፣ ቸነፈርንም እሰድዳለሁ።"
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።