መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኤርሚያስ 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ሆይ፣ ከአንተ ጋር በተሟገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ። የማጉረመርምበትን ምክንያት በእርግጥ ልነግርህ ይገባኛል። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይሳካል? እምነት-የለሽ የሆኑት ሁሉ ተሳክቶላቸዋል።
2አንተ ተክለሃቸዋል፣ እነርሱም ሥር ሰድደዋል። ፍሬ ማፍራታቸውን ቀጥለዋል። በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፣ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።
3ይሁን እንጂ አንተ እግዚአብሔር ታውቀኛለህ። አይተኸኛል፣ ልቤንም ፈትነሃል። እንደ ሚታረዱ በጎች ለያቸው። ለመታረድም ቀን ነጥላቸው።
4ምድሪቱ የምታለቅሰው፣ የአገሩ ሣርስ ሁሉ ከነዋሪዎቹ ክፋት የተነሣ የሚደርቀው እስከ መቼ ነው? አራዊት እና ወፎች ተወስደዋል። በእርግጥም ሕዝቡ "በእኛ ላይ የሚሆነውን እግዚአብሔር አያውቅም፤" ብለዋል።
5"አንተ ኤርምያስ ከእግረኛ ወታደሮች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፣ ከፈረሶች ጋር መወዳደር እንዴት ትችላለህ? በአስተማማኝ የገጠር ምድር ውስጥ ብትሰናከል፣ በዮርዳኖስ ጥሻዎች ውስጥ እንዴት ትሆናለህ?
6ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አሳልፈው ሰጥተውሃልና፣ ጮኸው ክደውሃልና። መልካም ነገሮችንም ቢናገሩህ አትታመናቸው።
7ቤቴን ትቼአለሁ፣ ርስቴንም ጥያለሁ። ተወዳጁን የገዛ ሕዝቤን በጠላቶቹ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።
8ርስቴ በጥሻ እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋን አንሥታብኛለችና ስለዚህ ጠልቻታለሁ።
9ርስቴ እንደ ጅብ ሆነችብኝ፣ ዝንጕርጕር አሞሮችም ለማጥመድ በላይዋ ይዞራሉ። ሂዱ፣ የምድር አራዊትን ሁሉ ከሜዳ ሰብስቡና ይበሉም ዘንድ አምጡአቸው።
10ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን ደምስሰዋል። እድል ፈንታዬ የሆነውን ምድር ሁሉ ረግጠዋል፤ የምደሰትበትን እድል ፈንታ ወና ምድረ በዳ አድርገውታል።
11ባድማ አድርገውታል። ፈርሳለችና አለቅስላታለሁ። ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት የለም።
12በወና ኮረብቶች ሁሉ ላይ አጥፊዎች መጥተዋል፣ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከአንደኛው የምድር ዳር ጀምሮ እስከ ሌላኛው የምድር ዳር ድረስ ይበላልና። በሕይወት ላለ ሥጋ ለባሽ ሁሉ ደህንነት የለም።
13ስንዴን የዘሩ ቢሆንም እሾህን አጨዱ። በሥራቸው ደከሙ፣ ምንም አላገኙም። ስለዚህ ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባገኛችሁት ፍሬ ታፍራላችሁ።
14ሕዝቤ እስራኤል እንዲወርስ ያደረግሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጐረቤቶች ሁሉ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ከገዛ ምድራቸው የምነቅላቸው እኔ ነኝ፣ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።
15ከነቀልኋቸውም በኋላ መልሼ እራራላቸዋለሁ፣ እያንዳንዱንም ወደ ርስቱ እያንዳንዱንም ወደ ምድሩ እመልሳለሁ።
16በበኣል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩት ሁሉ እነዚያው ሕዝቦች 'ሕያው እግዚአብሔርን!' ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ በጥንቃቄ ቢማሩ፣ በዚያን ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ።
17ነገር ግን ማናቸውም ባይሰሙኝ ያንን ሕዝብ ፈጽሜ እነቅለዋለሁ። በእርግጥም ይነቀላል፣ ይጠፋማል" ይላል እግዚአብሔር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።