1ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ።
2የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስማ፣ ለእያንዳንዳቸው የይሁዳ ሰዎች፣ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩትም ተናገር፥
3እንደዚህም በላቸው 'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የዚህን ቃል ኪዳን ቃል የማይሰማ ሰው ርጉም ይሁን።
4ከግብጽ አገር ከሚቀልጠው የብረት ምድጃ ባወጣኋቸው ቀን ለአባቶቻችሁ ያዘዝሁበት ኪዳን ይህ ነው። "ድምፄን ስሙ፣ ያዘዝኋችሁንም ነገሮች ሁሉ አድርጉ፣ እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁና።"
5ይህም ዛሬ የምትኖሩባትን ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻችሁ የማልሁትን መሐላ አጸና ዘንድ ነው።" ከዚያ እኔ ኤርምያስ "አዎን፣ እግዚአብሔር ሆይ!' ብዬ መለስሁለት።
6እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ "ይህችን ቃል ሁሉ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ተናገር። እንዲህ በል፣ 'የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ ፈጽሙትም።
7አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ "ቃሌን ስሙ" በማለት በጽናት አስጠንቅቄአቸው ነበር።
8እነርሱ ግን አልሰሙም ወይም ትኩረት አልሰጡም። እያንዳንዱ ሰው በክፉ ልባቸው እልከኝነት ሄዱ። ስለዚህ እንዲመጡባቸው ያዘዝኋቸውን እርግማን ሁሉ አመጣሁ። ሕዝበ ግን እንደዚያም ሆኖ አልታዘዙም።"
9ቀጥሎ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ "በይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ዘንድ አድማ ተገኝቶአል።
10ቃሌንም ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወዳሉ፣ ይልቊንም ያመልኩአቸው ዘንድ እንግዶችን አማልክት ወደተከተሉ ወደ አባቶቻቸው ኃጢአት ተመለሱ። የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፈረሱ።
11ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ሊያመልጡት የማይችሉትን ጥፋት አመጣባቸዋለሁ። ከዚያም ወደ እኔ ይጮኻሉ፣ እኔ ግን አልሰማቸውም።
12የይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩት ሄደው ወደሚሰዉላቸው አማልክት ይጮኻሉ፤ ነገር ግን በጥፋታቸው ጊዜ ከቶ አያድኑአቸውም።
13ይሁዳ፣ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ጨምረዋል። በኢየሩሳሌምም መንገዶች ቍጥር ልክ አሳፋሪ መሠዊያ፣ ለበዓለም የማጠኛ መሠዊያ አድርጋችኋል።
14ስለዚህ አንተ ራስህ፣ ኤርምያስ፣ ለዚህ ሕዝብ ልትጸልይ አይገባም። ስለእነርሱ አታልቅስ ወይም አትጸልይ። በጥፋታቸው ጊዜ ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውምና።
15እጅግ ብዙ ክፉ ፍላጎት የነበረው ተወዳጁ ሕዝቤ በቤቴ ውስጥ ያለው ለምንድነው? ለመስዋዕታችሁ የተጠበቀው ሥጋ ክፋትን አድርጋችኋልና ሊረዳችሁ አይችልም፣ ከዚያም በዚያ ደስተኛ አትሆኑም።
16በጥንቱ ጊዜ እግዚአብሔር በተወዳጅ ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎ ጠራሽ። ሆኖም ግን እንደ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፣ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል።
17ለበኣልም በማጠናቸው ያስቈጡኝ ዘንድ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉን ነገር ተናግሮብሻል።
18እግዚአብሔርም እነዚህን ነገሮች አውቃቸው ዘንድ አስታወቀኝ፤ አንተ እግዚአብሔር ሥራቸውን እንዳይ አደረግኸኝ።
19እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ የበግ ጠቦት ሆንሁ። እነርሱም፣ "ዛፉን ከፍሬው ጋር እንቍረጥ! ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው" ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
20ይሁን እንጂ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አእምሮንና ልብን ይመረምራል፣ በቅንም ይፈርዳል። ጉዳዬን አቅርቤልሃለሁና በእነርሱ ላይ በቀልህን እመሰክራለሁ።
21ስለዚህም 'በእጃችን እንዳትሞት በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር' ብለው ነፍስህን ስለሚሹ ስለ ዓናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
22ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህንን ይላል፣ 'ተመልከት፣ እቀጣቸዋለሁ። ኃያላን ወጣቶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በረሃብ ይሞታሉ።
23በምቀጣቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚቀር የለም።