መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ያዕቆብ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ወንድሞቼ፣ እኛ የባሰውን ፍርድ እንደምንቀበል በመገንዘብ፣ ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አትሁኑ።
2ሁላችንም በብዙ መንገድ እንሰናከላለን። በንግግሩ የማይሰናከል እርሱ ሰውነቱን ሁሉ መቆጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው።
3ፈረሶች አፍ ውስጥ ልጓም ብናደርግ ይታዘዙልናል፤ መላ አካላቸውንም መቆጣጠር እንችላለን።
4ምንም እንኳ መርከቦች ግዙፍና በኃይለኛ ነፋስ የሚነዱ ቢሆኑም፣ የመርከቡ ነጂ በትንሽ መሪ ወደሚፈልገው አቅጣጫ እንደሚመራቸው አስተውሉ።
5እንዲሁም አንደበት ትንሽ የሰውነት ክፍል ሆኖ፣ በታላላቅ ነገሮች ይኵራራል። ጫካ የቱንም ያህል ሰፊ ቢሆን፣ በትንሽ እሳት ፍንጣሪ እንደሚቃጠል ልብ አድርጉ!
6አንደበትም እንዲሁ እሳት ነው፤ ሰውነትን ሁሉ የሚያረክስና የሕይወትንም መንገድ የሚያቃጥል፣ እርሱ ራሱም በገሃነም እሳት የሚቃጠል ሰውነታችን ብልቶች መካከል ያለ ኃጢአተኛ ዓለም ነው።
7ማንኛውም እንስሳ፣ ወፎች፣ በምድር የሚሳቡና ባሕር ውስጥ ያሉ ፍጥረቶች በሰው ተገርተዋል፤
8ነገር ግን ከሰው መካከል ማንም አንደበትን መግራት አልቻለም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ዕረፍት የለሽ ክፉ ነው።
9በአንደበት ጌታና አባታችንን እንባርካለን፤ በዚያው አንደበት በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን።
10ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣል። ወንድሞቼ፣ እንዲህ መሆን የለበትም።
11ከአንድ ምንጭ ጣፋጭና መራራ ውሃ ይወጣልን?
12ወንድሞቼ፣ የበለስ ዛፍ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ያበቅላልን? እንዲሁም ከጨው ውሃ ንጹሕ ውሃ ሊገኝ አይችልም።
13ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? ያ ሰው ከጥበብ በሚገኝ ትሕትና በሥራው መልካም ሕይወትን ያሳይ።
14በልባችሁ መራራ ቅናትና ራስ ወዳድ ምኞት ካለ ግን አትኵራሩ፤ በእውነትም ላይ አትዋሹ።
15ይህ ከላይ የሚመጣ ጥበብ አይደለም፤ ይልቁንም ምድራዊ፣ መንፈሳዊ ያልሆንና አጋንንታዊም ነው።
16ምክንያቱም ቅናትና ራስ ወዳድ ምኞት ባለበት ሁከትና ክፉ ሥራ ይኖራል።
17ከላይ የሚመጣው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ከዚያም ሰላም ወዳድ፣ ጨዋ፣ ደግ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላበት፣ ለሰዎች አድልዎ የማያደርግ ቅን ነው።
18ሰላምን ለሚያደርጉ የጽድቅ ፍሬ በሰላም ይዘራል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።