መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢሳይያስ 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት፣ እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፣ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።
2ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፣ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፣ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።
3አንዱም አንደኛውን በመጥራት፣ "ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር! ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች" እያለ ይጮኽ ነበር።
4የመድረኩም መሠረት ከሚጮኹት ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፣ ቤቱም ጢስ ሞላበት።
5ከዚያ እኔ፣ "ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፣ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ፣ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!" አልሁ።
6ከዚያም ከሱራፌል አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፤ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ።
7በዚያም አፌን ዳሰሰበትና። "ተመልከት፣ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፣ ኃጢአትህም ተሰረየልህ።" አለኝ።
8የጌታንም ድምፅ፣ "ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?" ሲል ሰማሁ። እኔም፣ "እኔ አለሁ፤ እኔን ላከኝ።" አልሁ።
9እርሱም፣ "ሂድና ይህን ሕዝብ፣ ትሰማላችሁ፣ አታስተውሉምም፤ ታያላችሁ፣ አትመለከቱምም" በላቸው።
10በዓይናቸው እንዳያዩ፣ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፣ ተመልሰውም እንዳይፈወሱ፣ የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፣ ጆሮአቸውንም አደንቍር፣ ዓይናቸውንም አሳውር" አለኝ።
11ከዚያም እኔ፣ "ጌታ ሆይ፣ እስከ መቼ ድረስ ነው?" አልሁ። እርሱም ሲመልስ፣ "ከተሞች የሚኖርባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፣ ቤቶችም ሰው የሌለባቸው እስኪሆኑ፣ ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ፣
12እግዚአብሔርም ሰዎችን እስኪያርቅ፣ በምድርም መካከል ውድማው መሬት እስኪበዛ ድረስ ነው።" አለ።
13በእርስዋም ዘንድ አንድ ዐሥረኛ ሰው ቀርቶ እንደ ሆነ እነርሱ ደግሞ በድጋሚ ይቃጠላሉ፤ በተቈረጡ ጊዜ ጉቶቻቸው እንደ ቀሩ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሆኖ፣ ጉቶው የተቀደሰ ዘር ይሆናል።"
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።