1በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች "የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ ውርደታችንንም አርቅ" ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።
2በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቍጥቋጥ ውብና የከበረ ይሆናል፣ ከእስራኤልም ወገን ላመለጡ ሰዎች የምድሪቱን ፍሬ ለትምክሕትና ለውበት ይሆናል።
3ከዚያም፣ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት እድፍ ባጠበ ጊዜ፣ የኢየሩሳሌምንም ደም በፍርድ መንፈስና በሚያቃጥል መንፈስ ከመካከልዋ ባነጻ ጊዜ፣
4በጽዮን የቀረ በኢየሩሳሌምም የተረፈ፣ በኢየሩሳሌም ለሕይወት የተጻፈ ሁሉ፣ ቅዱስ ይባላል።
5እግዚአብሔርም በጽዮን ተራራ ላይ ባለ ማደሪያ ሁሉ በጉባኤያቸውም ላይ፣ በቀን ዳመናንና ጢስን፣ በሌሊትም የሚቃጠለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብርም ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል።
6በቀን ከሙቀት ለጥላ፣ ከዐውሎ ነፋስና ከዝናብም ለመጠጊያና ለመሸሸጊያ ጎጆ ይሆናል።