መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢሳይያስ 39

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በዚያ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን፣ ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት።
2ሕዝቅያስም በእነዚህ ነገሮች ደስ አለው፣ ግምጃ ቤቱንም፣ ብሩንና ወርቁንም፣ ቅመሙንና የከበረውንም ዘይት፣ መሣርያም ያለበትን ቤት ሁሉ፣ በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።
3ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፣ "እነዚህ ሰዎች ምን አሉህ? ከወዴትስ መጡ?" አለው። ሕዝቅያስም፣ "ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡልኝ" አለው።
4እርሱም፣ "በቤትህ ያዩት ምንድር ነው?" አለው። ሕዝቅያስም፣ "በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በቤተ መዛግብቴ ካለው ያላሳየኋቸው የለም" አለው።
5ኢሳይያስም ሕዝቅያስን፣ "የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።
6'ተመልከት፣ በቤትህ ያለው ሁሉ፣ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ፣ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል። ምንም አይቀርም፥ ይላል እግዚአብሔር።
7ከአንተም ከሚወለዱት ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ" አለው።
8ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፣ "የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው" አለው። ደግሞም፣ "በዘመኔ ሰላምና እውነት ይሁን" አለ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።