መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢሳይያስ 31

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፣ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፣ (እጅግ ብርቱዎችም) ስለ ሆኑ፣ በፈረሰኞች ለሚታመኑ (የማይቆጠሩ ስለሆኑ) ፣ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ እግዚአብሔርንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!
2እርሱ ደግሞ ጠቢብ ነው፣ ክፉንም ነገር ያመጣል፣ ቃሉንም አይመልስም። በክፉም አድራጊዎች ቤት ላይ በደልንም በሚሠሩ ረዳት ላይ ይነሣል።
3ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፣ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም። እግዚአብሔርም እጁን በዘረጋ ጊዜ፣ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፣ ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
4እግዚአብሔር የሚለኝ እንዲህ ነውና፣ "አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ ሲያገሳ፣ ብዙ እረኞች ቢከማቹበት ከቃላቸው እንደማይፈራ፣ ከድምፃቸውም እንደማይዋረድ፣ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።
5እንደሚበርር ወፍ፣ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፥ በላይዋ ሲያልፍ ይታደጋታል ያድናታልም።
6እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፣ አጥብቃችሁ ወደ ዐመፃችሁበት ተመለሱ።
7በዚያም ቀን እያንዳንዳቸው እጆቻቸው ለኃጢአት የሠሩላቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ይጥላሉና።
8አሦርም በሰይፍ፣ የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፣ የሰውም ያልሆነ ሰይፍ ይበላዋል፤ ከሰይፍም ይሸሻሉ ጐበዛዝቱም ገባሮች ይሆናሉ።
9አምባው ከፍርሃት የተነሣ ያልፋል፣ መሳፍንቱም ከዓላማው የተነሣ ይደነግጣሉ፤" ይላል እሳቱ በጽዮን፣ እቶኑም በኢየሩሳሌም የሆነ እግዚአብሔር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።