መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢሳይያስ 29

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ዳዊት ሰፍሮባት ለነበረችው ከተማ ለአርኤል፣ ወዮላት! ዓመት በዓመት ላይ ጨምሩ፣ በዓላትም ተመልሰው ይምጡ።
2ነገር ግን አርኤልንም እከብባለሁ፣ ለቅሶና ዋይታም ይሆንባታል፤ ለእኔም እንደ አርኤልም ትሆንልኛለች።
3በዙሪያሽም እሰፍራለሁ፣ በቅጥርም ከብቤ አስጨንቅሻለሁ፣ አምባም በላይሽ አቆማለሁ።
4ትዋረጂማለሽ፣ በመሬትም ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፣ ቃልሽም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፤ ድምፅሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምፅ ይሆናል፣ ቃልሽም ከአፈር ወጥቶ በደካማነት ይጮኻል።
5ነገር ግን የጠላቶችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፣ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል። በድንገት፣ በፍጥነትም ይሆናል።
6የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፣ በምድርም መናወጥ፣ በታላቅም ድምፅ፣ በዐውሎ ነፋስም፣ በወጨፎም፣ በምትባላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።
7በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፣ እርስዋንና ምሽግዋንም የሚወጉ የሚያስጨንቋትም፣ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደ ሕልምና እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል። ሊያስጨንቋት እርሷንና ምሽጎቿን ያጠቃሉ።
8የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ እንደሚያይ፣ ነገር ግን ሲነቃ ሆዱ ባዶ እንደሆነው ያክል ነው። የተጠማም ሰው በሕልሙ እየጠጣ እንደሚያይ፣ ነገር ግን ሲነቃ ጥሙ ሳይቆርጥለት ይዝላል። እንዲሁ የጽዮንን ተራራ የሚወጉ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት ይሆናል።
9ለራሳችሁ ተደነቁ፣ ተገረሙም፤ ራሳችሁን አሳውሩ፣ የታወራችሁ ሁኑ! በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ሰከሩ፤ በሚያሰክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገደገዱ።
10እግዚአብሔር የጥልቅ እንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል። ዐይኖቻችሁን አጨፍኗል፣ ራሶቻችሁን ደግሞ ነቢያት አጨፍነውባችኋል።
11ራእይ ሁሉ እንደ ታተመ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፤ ማንበብንም ለሚያውቅ። ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ። ታትሞአልና አልችልም ይላቸዋል፤
12ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ "ይህን አንብብ" ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፣ "ማንበብ አልችልም" ይላቸዋል።
13ጌታም አለ፣ "ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፣ በከንፈሮቹም ያከብረኛልና፣ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው። የሚያከብሩኝ ሰዎች ባስተማሩት ትእዛዝ ነው።
14ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል ለማድረግ እቀጥላለሁ፤ ድንቅ ነገርን በድንቅ ነገር ላይ አደርጋለሁ። የጥበበኞቻቸውም ጥበብ ትጠፋለች፣ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።"
15ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፣ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፣ "ማን ያየናል፣ ወይስ ማን ያውቀናል?" ለሚሉ ወዮላቸው!
16ነገሮችን ገለባብጣችኋል! የተሠራው ነገር የሠራውን "አልሠራኝም፣" ይለው ዘንድ ሸክላ ሠሪው እንደ ጭቃው ሊቆጠር ይገባልን? ወይስ የተበጀው ነገር ያበጀውን "አታስተውልም" ይለዋልን?
17ሊባኖስ እንደ ፍሬያማ እርሻ ሊለወጥ ፍሬያማውም እርሻ እንደ ዱር ሊቈጠር ጥቂት የቀረው አይደለምን?
18በዚያም ቀን ደንቆሮች የመጽሐፍን ቃል ይሰማሉ፣ የዕውሮችም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተለይተው ያያሉ።
19የተጨቆኑ ደስታቸውን በእግዚአብሔር ያበዛሉ፣ በሰዎች መካከል ያሉ ድሆችም ሐሤትን በእስራኤል ቅዱስ ያደርጋሉ።
20ጨካኙ ይቋረጣልና፣ ፌዘኛውም ይጠፋልና። ክፋትን ማድረግ የሚወድዱ ይወገዳሉ።
21እነዚህም ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ። በበርም ለሚገሥጸው ወጥመድ የሚያኖሩ፣ ጻድቁንም በከንቱ ውሸት የሚያስቱ ናቸው።
22ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠ እግዚአብሔር ስለ ያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፣ "ያዕቆብ ከእንግዲህ አያፍርም፣ ፊቱም አይገረጣም።
23ነገር ግን የእጄ ሥራ የሆኑትን ልጆቹን ባያቸው ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ። የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፣ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ።
24በመንፈስም የሳቱ ማስተዋልን ያገኛሉ፣ የሚያጕረመርሙም ትምህርትን ይቀበላሉ።"
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።