መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢሳይያስ 27

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በዚያም ቀን እግዚአብሔር ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን ጠማማውንም እባብ ሌዋታንን በጠንካራ፣ በታላቅ፣ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፥ በባሕርም ውስጥ ያለውን አውሬ ይገድላል።
2በዚያም ቀን፣ ለተወደደው የወይን ቦታ ተቀኙለት።
3"እኔ፣ እግዚአብሔር ጠባቂው ነኝ፤ ሁልጊዜ አጠጣዋለሁ፤ ማንም እንዳይጐዳው በሌሊትና በቀን እጠብቀዋለሁ።
4እሾህና ኵርንችት ለሰልፍ በመኖራቸው አልተቈጣሁም! በውጊያ በእነርሱ ላይ ተራምጄ፣ በአንድነት ባቃጠልኋቸው ነበር።
5ከለላነቴን ካልያዙና ከእኔ ጋር ሰላም ካላደረጉ፣ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርጉ።
6በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፣ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።"
7በውኑ የመቱትን እንደ መታ እንዲሁ እርሱን መታውን? ወይስ እነርሱ እንደ ተገደሉበት መገደል ያዕቆብና እስራኤል ተገድሎአልን?
8ያዕቆብና እስራኤልን ለማባረር በታገልክበት መጠን፣ እርሱ ነዳቸው ሰደዳቸው ቀሠፋቸው፤ የምሥራቅ ነፋስ በሚነፍስበት ቀን በጠንካራ ዐውሎ ነፋስ አስወገዳቸው።
9ስለዚህም በዚህ መንገድ፣ የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፣ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፣ ይህም ከኀጢአት የመመለስ ፍሬ ሁሉ ነው።
10የተመሸገችው ከተማ ጠፋች፣ እንደ ምድረ በዳ የተፈታችና የተተወች መኖሪያ ናት። በዚያም ጥጃ ይሰማራል፣ በዚያም ይተኛል ቅርንጫፍዋንም ይበላል።
11ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ። ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
12በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ ምንጭ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ እህሉን ይወቃል፥ እናንተም የእስራኤል ሕዝቦች ሆይ፣ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
13በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፣ በአሦርም የጠፉ፣ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፣ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ይሰግዳሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።