1የአሦር ንጉሥ ሳርጎን ተርታንን በሰደደ ጊዜና ወደ አዛጦን በመጣ ጊዜ አዛጦንም ወግቶ በያዛት ጊዜ፥
2በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፣ "ሂድና ማቅህን ከወገብህ አውጣ፣ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ" ብሎ ተናገረው። እንዲህም አደረገ፣ ራቁቱንም ባዶ እግሩንም ሄደ።
3እግዚአብሔርም አለ፣ "ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፣
4በዚህ መንገድ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፣ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፣ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፣ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል።
5እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል፤
6በዚያም ቀን በዚች ባሕር ዳርቻ የሚኖሩ፣ "በእርግጥ፣ ከአሦር ንጉሥ እንድን ዘንድ ለእርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፤ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?" ይላሉ።