መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢሳይያስ 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ ያያቸው ነገሮች።
2በኋለኞቹ የፍጻሜ ቀናት፣ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ከፍታ ላይ ጸንቶ ይቆማል፣ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይጎርፋሉ።
3ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፣ "ኑ፣ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ።"
4በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፣ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፣ ጦርነትንም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።
5እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ኑ፣ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ።
6የምሥራቅን ሰዎች አመል ስለ ተሞሉ፣ እንደ ፍልስጥኤማውያንም ምዋርተኞች ስለ ሆኑ፣ ከባዕድ ልጆችም ጋር ስለ ተባበሩ፣ የሕዝብህን የያዕቆብን ቤት ትተሃል።
7ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፣ ለመዛግብቶቻቸውም ፍጻሜ የለውም፤ ምድራቸውም ደግሞ በፈረሶች ተሞልታለች፣ ለሠረገሎቻቸውም ፍጻሜ የለውም።
8ምድራቸው ደግሞ በጣዖታት ተሞልታለች፤ ጣቶቻቸውም ላደረጉት ለእጃቸው ሥራ ይሰግዳሉ።
9ታናሹም ሰው ዝቅ ብሎአል፣ ግለሰቦችም ይዋረዳሉ፤ ስለዚህ አትቀበላቸው።
10ከእግዚአብሔር ማሸበርና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻ ግቡ፣ በመሬትም ውስጥ ተሸሸጉ።
11ከፍ ያለችውም የሰው ዓይን ትዋረዳለች፣ የሰዎችም ኵራት ተጎትታ ትወድቃለች፣ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ይላል።
12የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ፣ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፣ እርሱም ይዋረዳል፤
13ደግሞም በረጅሙ ከፍ ባለው በሊባኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፣ በባሳንም ዛፍ ሁሉ ላይ ይሆናል፣
14በረጅሞቹም ተራራዎች ሁሉ ላይ፣ ከፍ ባለውም ኮረብቶች ሁሉ ላይ፣
15በረጅሙም ግንብ ሁሉ ላይ፣ በተመሸገውም ቅጥር ሁሉ ላይ፣
16በተርሴስም መርከቦች ሁሉ ላይ፣ በሚያማምሩ ጣዖታትም ሁሉ ላይ ይሆናል።
17የሰው ሁሉ ክብር ይዋረዳል፣ የሰውም ኵራት ይወድቃል፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።
18ጣዖቶቻቸውም ሁሉ ፈጽመው ይጠፋሉ።
19እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ፣ ሰዎችን ከማስደንገጡና ከግርማው ክብሩ የተነሣ፣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃቃት ውስጥ ይገባሉ።
20በዚያን ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላሉ።
21እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ከማስደንገጡና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ተሰነጠቁ ዓለቶች ውስጥ ይገባሉ።
22እስትንፋሱ በአፍንጫው ውስጥ ያለበትን ሰው ተዉት፣ እርሱ ስለ ምን ይቈጠራል?
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።