መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢሳይያስ 13

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ያየው ስለ ባቢሎን የተነገረ ሸክም።
2ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምልክትን አቁሙ፣ ድምፅንም ከፍ አድርጉባቸው፤ በአለቆችም ደጆች እንዲገቡ እጃችሁን አንስታችሁ አሳዩ።
3ቍጣዬን ይፈጽሙ ዘንድ ቅዱሳኔን አዝዣለሁ፣ እኔ ኃያላኔንና በታላቅነቴ ደስ የሚላቸውን ጠርቻለሁ።
4በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ! የተከተማቹት የአህዛብ መንግሥታት የውካታ ጫጫታ አለ! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊትን ለሰልፍ አሰልፎአል።
5እግዚአብሔርና የቍጣው የጦር ዕቃ ምድርን ሁሉ ያጠፉአት ዘንድ ከሩቅ አገር፣ ከሰማይ ዳርቻ ይመጣሉ።
6የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፣ አልቅሱ፤ ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደሚመጣ ጥፋት ይመጣል።
7ስለዚህ፣ እጅ ሁሉ ትዝላለች፣ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል፤
8ይደነግጣሉ፤ ምጥና ሕማም ይይዛቸዋል፣ እንደምትወልድ ሴትም ያምጣሉ። አንዱም በሌላው ይደነቃል፣ ፊታቸውም የነበልባል ፊት ነው።
9ተመልከቱ፣ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፣ ኃጢአተኞችዋንም ከእርስዋ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቍጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል።
10የሰማይም ከዋክብትና ሠራዊቱ ብርሃናቸውን አይሰጡም፣ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፣ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም።
11ዓለሙን ስለ ክፋታቸው ክፉዎቹንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ። የእብሪተኞችንም ኵራት፣ የጨካኞቹንም ትዕቢት አዋርዳለሁ።
12የቀሩትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከበሩ ይሆናሉ፣ ሰውም ከኦፊር ወርቅ ይልቅ የከበረ ይሆናል።
13ስለዚህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት፣ በጽኑ ቍጣ ቀንም ሰማያትን አነቃንቃለሁ፣ ምድርም ከስፍራዋ ትናወጣለች።
14እንደ ተባረረም ሚዳቋ፣ ማንም እንደማይሰበስበው እንደ በግ መንጋ፣ ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመለሳል፣ ሁሉም ወደ አገሩ ይሸሻል።
15የተገኘ ሁሉ ይገደላል፣ የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይሞታል።
16ሕፃናቶቻቸውም በዐይናቸው ፊት እስኪቆራረጡ ድረስ ይጨፈጨፋሉ። ቤቶቻቸውም ይበዘበዛሉ፣ ሚስቶቻቸውም ተይዘው ይነወራሉ።
17ተመልከቱ፣ ብር የማይሹትን፣ ወርቅም የማያምራቸውን ሜዶናውያንን በላያቸው አናውጣለሁ።
18ፍላጾቻቸውም ጎበዞችን ይወጋሉ። ጨቅላዎችን አይምሩም፣ ዓይኖቻቸውም ለሕፃናት አይራሩም።
19እግዚአብሔርም ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደ ነበረው፣ የመንግሥታት ክብር፣ የከለዳውያንም ትዕቢት ጌጥ ባቢሎን እንዲሁ ትሆናለች።
20ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ማንም ሰው አይኖርባትም፤ ዓረቦቹ ድንኳንን በዚያ አይተክሉም፣ እረኞችም መንጎቻቸውን በዚያ አያሳርፉም።
21በዚያም የምድረ በዳ አራዊት ያርፋሉ። ጕጕቶችም በቤቶቻቸው ይሞላሉ፤ ሰጎኖችና የበረሃ ፍየሎች በዚያ ይኖራሉ።
22ጅቦችም በግንቦቻቸው፣ ቀበሮችም በሚያማምሩ አዳራሾቻቸው ይጮኻሉ። ጊዜዋም ለመምጣት ቀርቦአል ቀንዋም አይዘገይም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።