1በዚያም ቀን፣ "እግዚአብሔር ሆይ፣ አመሰግንሃለሁ። ተቈጥተኸኛልና፣ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፣ አጽናንተኸኛልምና።
2ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፣ አዎን፣ በእርሱ ታምኜ አልፈራም። መድኃኒቴም ሆኖአልና" ትላለህ።
3ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ።
4በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፣ "እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ሥራውን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ ተናገሩ።
5ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና ለእግዚአብሔር ተቀኙ፤ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ የታወቀ እንዲሆን አድርጉ።
6አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፣ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና ደስ ይበልሽ እልልም በዪ።"