መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሆሴዕ 9

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እስራኤል ሆይ፥ አንተ የታመንክ አይደለህምና፥ አምላክህንም ትተሃልና፤ ሌሎች ሕዝቦች ደስ እንደሚላቸው፥ ደስ አይበልህ። በአውድዎች ሁሉ ላይ ሴተኛ አዳሪ የምትጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ወድደሃል።
2ነገር ግን አውድማውና የወይን መጭመቂያው አይመግባቸውም፥ አዲሱ የወይን ጠጅም ይጥላታል።
3በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይኖሩም፤ ኤፍሬም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ ደግሞም አንድ ቀን በአሦር የረከሰ ምግብ ይበላሉ።
4ለእግዚአብሔር የወይን ጠጅ ቁርባን አያፈሱም፤ ደስም አያሰኙትም። መስዋዕታቸው እንደ ሐዘንተኞች ምግብ ይሆንባቸዋል፦ የሚበሉት ሁሉ ይረክሳሉ። ምግባቸው ለእነርሱ ብቻ የሚሆን ነውና ወደ እግዚአብሔር ቤት ሊመጣ አይችልም።
5በእግዚአብሔር በዓል ቀን፥ በዓመት በዓል ቀን ምን ታድርጋላችሁ?
6ተመልከቱ፥ ከጥፋት ቢያመልጡ እንኳን ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፥ ሜፎስም ትቀብራቸዋለች። የብር ክምችታቸውን ሳማ ይውጠዋል፥ድንኳኖቻቸውንም እሾህ ይሞላዋል።
7የቅጣት ቀን እየመጣ ነው፥የበቀል ቀን እየመጣ ነው። እስራኤል ሁሉ ይህን ይወቅ። ከክፋትህና ከጠላትነትህ የተነሳ፤ ነቢዩ ሞኝ፥ በመንፈስ የሚነዳውም ሰው እብድ ሆኖእል።
8ከአምላኬ ጋር የሆነው ነቢይ የኤፍሬም ጠባቂ ነው፤ ነገር ግን የወፍ ወጥመድ በመንገዱ ሁሉ ነው፥በአምላኩም ቤት ጠላትነት አለበት።
9በጊብዓ ዘመን እንደነበረው ራሳቸውን እጅግ አርክሰዋል። እግዚአብሔር ክፋታቸውን ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይቀጣል።
10እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥«እስራኤልን ያገኘሁበት ጊዜ፥ በምድረ በዳ ወይን እንደማግኘት ነበረ። እንደ በለስ ዛፍ የፍሬ ጊዜ የመጀመሪያ እሸት አባቶቻችሁን አገኘሁ።ነገር ግን ወደ ብዔልፌጎር ሄዱ፥ራሳቸውንም ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ሰጡ።እንደወደዱት ጣዖት እነርሱም የተጠሉ ሆኑ።
11የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይሄዳል።መውለድ፥ ማርገዝና መፀነስ የለም።
12ልጆችን ቢያሳድጉ እንኳን፥ አንዳቸውም እሰከማይቀሩላቸው ድረስ እወስድባቸዋለሁ። ከእነርሱ ዘወር ባልሁ ጊዜ፥ ወዮ ለእነርሱ!
13ኤፍሬም እንደ ጢሮስ በለምለም ስፍራ ተተክሎ አየሁት፥ ነገር ግን ኤፍሬም ልጆቹን ለሚያርዳቸው አሳልፎ ይሰጣል።
14እግዚአብሔር ሆይ ስጣቸው፤ ምን ትሰጣቸዋለህ? የሚጨነግፍ ማኅፀንና ወተት የማይሰጡ ጡቶች ስጣቸው።
15በጌልጌላ ካደረጉት ክፋታቸው ሁሉ የተነሳ፥ በዚያ እነርሱን መጥላት ጀመርኩ። ከክፉ ሥራቸው የተነሣ፥ ከቤቴ አስወጣቸዋለሁ። ከእንግዲህ ወዲያ አልወዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመጸኞች ናቸው።
16ኤፍሬም በበሽታ ተመታ፤ሥራቸውም ደረቀ፥ ፍሬም አይሰጡም። ልጆች ቢወልዱም እንኳን፥ የተወደዱ ልጆቻቸውን እገድላለሁ።»
17አልታዘዙትምና አምላኬ ይጥላቸዋል። በሕዝቦች መካከል ተንከራታች ይሆናሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።