1«መለከትን በከንፈሮችህ ላይ አድርግ። በእኔ በእግዚአብሔር ቤት ላይ ንስር እየመጣ ነው። ሕዝቡ ኪዳኔን አፍርሰዋልና በሕጌም ላይ አምጸዋልና ይህ ይሆናል።
2'አምላኬ፥ በእስራኤል ያለን እኛ እናውቅሃለን' እያሉ ወደ እኔ ይጮሃሉ።
3ነገር ግን እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ጥሎአል፥ ጠላትም ያሳድደዋል።
4ነገሥታትን አነገሡ፥ በእኔ ግን አይደለም። እኔም ሳላውቅ መሳፍንቶችን አደረጉ። በብራቸውና በወርቃቸው ለራሳቸው ጣዖታትን ሠሩ፥ ነገር ግን ለጥፋታቸው ብቻ ነበር።»
5ነቢዩ፦«ሰማርያ ሆይ ጥጃህን ወዲያ ጥሎታል» አለ። እግዚአብሔር፦«ቁጣዬ በዚህ ህዝብ ላይ ነድዶአል። ሳይነጹ እስከ መቼ ይኖራሉ? አለ።
6ይህ ጣዖት ከእስራኤል የመጣ ነው፤ ባለሙያ ሠራው፥ እርሱ አምላክ አይደለም! የሰማርያ ጥጃ ይደቅቃል።
7ሕዝቡ ነፋስን ዘርተዋል፥ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ። ያልተሰበሰበው እህል ዛላ የለውም፤ ዱቄትም አይገኝበትም። ለማፍራት ቢደርስም እንኳን እንግዶች ይበሉታል።
8እስራኤል ተውጦአል፤ በአሕዛብም መካከል እንደማይጠቅም ነገር ወድቀዋል።
9ሁሌ ብቻውን እንደሚሆን የዱር አህያ፥ወደ አሦር ሄደዋልና። ኤፍሬም ለራሷ ወዳጆችን ገዛች።
10በአሕዛብ መካከል ወዳጆችን ቢገዙም፥ እኔ እሁን አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ። ከመሳፍንቱ ንጉሥ ጭ ቆና የተነሳም ሊመነምኑ ይጅምራሉ።
11ኤፍሬም ለኃጢአት ማስተሰሪያ መሠዊያ ቢያበዛም፥በዚያ ፈንታ ግን የኃጢአት መሥሪያ መሠዊያዎች ሆኑ።
12ሕጌን አሥር ሺህ ጊዜ ያህል ፃፍሁላቸው፥ እነርሱ ግን እንግዳ እንደ ሆነ ነገር ተመለከቱት።
13መሥዋዕቴን ይሠዋሉ፤ ሥጋ ይሠዋሉ፥ ይበሉታልም፤ እኔ እግዚአብሔር ግን አልተቀበልኳቸውም። አሁን ክፋታቸውን አስባለሁ፥ ኃጢአታቸውንም እቀጣለሁ። ወደ ግብጽ ይመለሳሉ።
14እስራኤል፥ እኔን ሠሪውን ረሳ፥ አብያተ መንግሥትንም ገነባ። ይሁዳ ብዙ ከተሞችን አጸና፥ እኔ ግን በከተሞቹ ላይ እሳት እሰድዳለሁ፤ ምሽጎቹንም ታጠፋለች።