መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሆሴዕ 7

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ማታለልን ይለማመዳሉና እስራኤልን ለመፈወስ በፈለግሁ ጊዜ ሁሉ የኤፍሬም ኃጢአት፥ የሰማሪያም ክፋት ይገለጣል፤ ሌባ ወደ ውስጥ ይገባል፥ የቀማኞች ቡድን በመንገድ ላይ አደጋ ያደርሳል።
2ክፋታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ በልባቸው አይገነዘቡም። ሥራቸው ከቦአቸዋል፥ በፊቴም ናቸው።
3በክፋታቸው ንጉሡን፥ በሐሰታቸውም አለቆቹን ደስ ያሰኛሉ።
4የተቦካው ሊጥ ኩፍ እስኪል ድረስ እሳቱን መቆስቆስ እንድሚያቆም፥ ጋጋሪ እንደሚያነድበት ምድጃ፥ ሁሉም አመንዝራ ናቸው።
5በንጉሣችን ቀን አለቆች በወይን ጠጅ ትኩሳት ታመሙ። እርሱም ለፌዘኞች እጁን ዘረጋ።
6እንደ ምድጃ በሆነ ልባቸው፥ አታላይ እቅዶቻችውን ይወጥናሉ። ቁጣቸው ሌሊቱን ሁሉ ይጤሳል፥ በማለዳም እንደሚንቀለቀል እሳት እጅጉን ይነድዳል።
7ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፥ ግዢዎቻቸውንም ይበላሉ። ነገሥታቶቻቸው ሁሉ ወደቁ፥ ከመካከላቸውም ማንም ወደ እኔ አልተጣራም።
8ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቅ፥ ኤፍሬም ያልተገለበጠ ቂጣ ነው።
9እንግዶች ጉልበቱን በሉት፥ እርሱ ግን አላወቀም። ሽበትም ወጣበት፥ እርሱ ግን አላወቀም።
10የእስራኤል ትዕቢት ይመሰክርበታል፤ ነገር ግን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር አልተመለሱም፥ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም።
11ኤፍሬም ማስተዋል እንደሌላትና ተላላ እንደ ሆነች ርግብ ነው፤ ወደ ግብጽ ይጣራል፥ ወደ አሦርም ይበራል።
12ሲሄዱ መሬቤን እዘረጋባቸዋለሁ፥ እንደ ሰማይ አዕዋፍ አወርዳቸዋለሁ። እንደ መንጋ በሚተምሙብት እቀጣቸዋለሁ።
13ወዮ ለእነርሱ! ከእኔ ርቀው ሄደዋልና። ጥፋት ይመጣባቸዋል! በእኔ ላይ አምፀዋል! ላድናቸው ወደድሁ፥ እነርሱ ግን ሐሰትን ተናገሩብኝ።
14ከልባቸው ወደ እኔ አይጮኹም፥ ነገር ግን በአልጋዎቻችው ላይ ያለቅሳሉ። እህልና አዲስ ወይን ጠጅ ለማግኘት ራሳቸውን ለይተዋል፥ ከእኔም ዘወር ብለዋል።
15እኔ ባሠለጠናቸውም፥ ክንዶቻችውንም ባበረታ፤ እነርሱ ግን ክፉ ነገርን አሴሩብኝ።
16ተመልሰዋል፥ ነገር ግን ወደ እኔ ወደ ልዑሉ አልተመለሱም። ዒላማውን እንደ ሳተ ቀስት ናቸው። ከምላሳቸው ነውረኛነት የተነሳ አለቆቻችው በሰይፍ ይወድቃሉ። ይህም በግብጽ ምድር ለመሳለቂያ ይሆንባቸዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።