1ኑ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ። እርሱ ገነጣጥሎናል፥ ነገር ግን እርሱ ይፈውሰናል፤ እርሱ አቁስሎናል፥ ነገር ግን እርሱ ቁስላችንን አስሮ ይጠግናል።
2ከሁለት ቀን በኋላ ያበረታናል፥ በሦሥተኛው ቀን ያሥነሣናል፥ እኛም በፊቱ እንኖራለን።
3አወጣጡ እንደ ንጋት የታመነ ነው፤ እንደ ካፊያ፥ ምድሪቱን እንደሚያጠጣ እንደ ጸደይ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።
4ኤፍሬም ሆይ ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ ምን ላድርግልህ? ታማኝነታችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በጠዋት እንደሚጠፋ ጤዛ ነው።
5ስለዚህ በነቢያቱ ቆራረጥኋቸው፥ በአፌም ቃል ገደልኋቸው። ፍርዶችህ እንደሚያንጸባርቅ ብርሃን ናቸው።
6ታማኝነትን እሻለሁና፥መሥዋዕትንም አይደለም፥ከሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ይልቅ እኔን እግዚአብሔርን ማወቅን እሻለሁ።
7እንደ አዳም ኪዳኑን አፍርሰዋል፤ ለእኔ ያልታመኑ ነበሩ።
8ገልዓድ የክፉ አድራጊዎች ከተማ ነው፥ በደም ዱካ ተሞልቷል።
9የቀማኞች ቡድን የሚዘርፉትን አድብተው እንደሚጠባበቁ፥ ካህናቱም በሴኬም መንገድ ላይ ሰው ለመግደል በቡድን ተደራጅተዋል፤ አሳፋሪም ወንጀል ይፈጽማሉ።
10በእስራኤል ቤት የሚያሰቅቅ ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ የኤፍሬም ምንዝርና አለ፥ እስራኤልም ተበክሏል።
11የሕዝቤን ምርኮ በምመልስበት ጊዜ፥ ይሁዳ ሆይ ለአንተም መከር ተቀጥሮልሃል።