መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሆሴዕ 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በእናንተ በሁላችሁ ላይ ፍርድ እየመጣ ነውና፤ ካህናት ሆይ ይህን ስሙ! የእስራኤል ቤት ሆይ ልብ በሉ! የንጉሡ ቤት ሆይ ስሙ! እናንተ፥ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋል።
2ዓመጸኞች በማረድ እጅግ በርትተዋል፥ ሁሉንም እገራቸዋለሁ።
3ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፥ እስራኤልም ከእኔ አልተሰወረችም። ኤፍሬም፥ አንተ አሁን እንደ ሴተኛ አዳሪ ሆነሃል፤ እስራኤልም ረክሳልች።
4ሥራቸው ወደ እኔ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፥ የአመንዝራነት መንፈስ በውስጣቸው አለ፥ እኔን እግዚአብሔርን አላወቁኝም።
5የእስራኤል ትዕቢት ይመሰክርባታል፤ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በበደላቸው ይሰናከላሉ፤ ይሁዳም ከእነርሱ ጋር ትሰናከላለች።
6በጎቻቸውንና ከብቶቸውን ይዘው እግዚአብሔርን ፍልጋ ይሄዳሉ፥ ነገር ግን ከእነርሱ ተለይቶ ተመልሷልና አያገኙትም።
7ዲቃሎች ልጆችን ወልደዋልና ለእግዚአብሔር ታማኞች አልሆኑም። አሁንም የወር መባቻ በዓላቱ እነርሱን ከእርሻቸው ጋር ይበሉአቸዋል።
8በጊብዓ መለከትን፥በራማም እንቢልታን ንፉ። «ቢንያም ሆይ እንከተልሃለን!» እያላችሁ የጦርነት ድምጽ አሰሙ።
9በቁጣው ቀን ኤፍሬም የፈረሰ ይሆናል። በእስራኤል ነገዶች መካከል በእርግጥ ሊሆን ያለውን አውጄአለሁ።
10የይሁዳ መሪዎች የድምበር ድንጋይ እንደሚነቅሉት ናቸው። ቁጣዬን በላያቸው እንደ ውኃ አፈስሳለሁ።
11ለጣዖታት ሊሰግድ ወስኖአልና ኤፍሬም ደቀቀ፥ በፍርድ ደቀቀ።
12እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፥ለይሁዳም ቤት እንደ ነቀዝ እሆናለሁ።
13ኤፍሬም በሽታውን ባየ ጊዜ፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ፤ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ይሁዳም ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኞችን ላከ። ነገር ግን እርሱ ሊያድናችሁ፥ ቁስላችሁንም ሊፈውስ አልቻለም።
14ስለዚህ በኤፍሬም ላይ እንደ አንበሳ፥ በይሁዳም ላይ እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁ። እኔ፥ አዎ እኔ፥ እገነጣጥላለሁ፥ እሄዳለሁ፥ እወስዳቸዋለሁ፥ የሚያድናቸውም ማንም የለም።
15በደላቸውን እስኪያውቁና ፊቴን እስኪፈልጉ ድርስ፥ በመከራቸው አጥብቀው እስኪፈልጉኝ ድረስ፥ እሄዳለሁ፥ ወድ ስፍራዬም እመለሳለሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።