መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሆሴዕ 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእስራኤል ሕዝብ ሆይ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። እውነተኛነት፥ ለኪዳን ታማኝነት፥ እግዚአብሔርን ማወቅ በምድሪቱ የለምና እግዚ አብሔር በምድሪቱ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለው።
2መርገም፥ መዋሽት፥ መግደል፥ መስረቅና ማመንዘር በዚያ አለ። ሕዝቡ ስምምነቶችን ሁሉ ያፈርሳሉ፥ ሳያቋርጡ ደም ይፋሰሳሉ።
3ስለዚህ ምድሪቱ ደረቀች፥ በእርሷ የሚኖሩ ሁሉ መነመኑ፥ የዱር አራዊትና የሰማይ አእዋፍ፥ የባሕርም ዓሦች እንኳን አለቁ።
4ነገር ግን ማንም ሙግቱን አያቅርብ፥ማንም ሌላውን ማንንም አይክሰስ። ምክንያቱም እኔ የምከስው እናንተን ካህናቱን ነውና።
5እናንተ ካህናት በቀን ትሰናከላላችሁ፥ ነቢያቶቹም ከእናንተ ጋር በሌሊት ይሰናከላሉ፥ እናታችሁንም አጠፋታለሁ።
6ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል። እናንተ ካህናት ዕውቀትን ጥላችኋልና እኔም እጥላችኋለሁ። እኔ አምላካችሁ ብሆንም ሕጌን ረስታችኋል፥ እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።
7ካህናቱ በበዙ መጠን የሚሠሩብኝ ኃጢአት በዝቶአል። ክብራቸውን ወደ ውርድት እለውጠዋለሁ።
8የሕዝቤን ኃጢአት ይመገባሉ፥ ክፋታቸውም እንዲበዛ ይቋምጣሉ።
9በካህናቱ ላይ እንደሚሆን እንዲሁ በሕዝቡም ላይ ይሆናል፦ ስለ ልማዶቻቸው እቀጣቸዋለሁ፤ እንደ ሥራቸውም አከፍላቸዋለሁ።
10ከእኔ ከእግዚአብሔር ርቀው ሄደዋልና ትተውኛልምና፤ይበላሉ ግን አይጠግቡም፥ ያመነዝራሉ ግን አይበዙም።
11ሴሰኝነት፥ የወይን ጠጅና አዲስ የወይን ጠጅ ማስተዋላቸውን ወስዶታል።
12የእንጨት ጣዖቶቻችውን ያማክራሉ፥ በትሮቻቸውም ይተነብዩላቸዋል። የሴሰኝነት መንፈስ አስቶአቸዋል፥ እኔን አምላካቸውንም ትተውኛል።
13በተራሮች ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፥ ጥላው መልካም ነውና ከባሉጥ፥ ከኮምቦልና ከአሆማ ዛፍ በታች በኮረብቶች ላይ ያጥናሉ። ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ የዝሙት ርኩሰት ይፈጽማሉ፥ የልጆቻችሁ ሚስቶች ያመነዝራሉ።
14ሴቶች ልጆቻችሁ የዝሙት ርኩሰትን በወደዱ ጊዜ፥ ወይም የልጆቻችሁ ሚስቶች ባመነዘሩ ጊዜ አልቀጣቸውም። ምክንያቱም ወንዶቹ ራሳቸውን ለሴተኛ አዳሪዎች ሰጥተዋልና፥ እንዲሁም ከቤተ ጣዖት ሴተኛ አዳሪዎች ጋር ርኩሰትን ለመፈጸም መሥዋዕት ይሰዋሉና። ስለዚህ ይህ የማያስተውል ሕዝብ ይጠፋል።
15እስራኤል ሆይ አንቺ ብታመነዝሪም፥ ይሁዳ በደለኛ አይሁን። እናንተ ሰዎች፥ ወደ ጌልጌላ አትሂዱ፥ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ። ሕያው እግዚአብሔርን ብላችሁም አትማሉ።
16እስራኤል እንደ እልኽኛ ጊደር በእልኽኝነት ሄዳለችና፤ እንዴት እግዚአብሔር በለመለመ መስክ እንዳ ሉ ጠቦቶች ያሰማራታል?
17ኤፍሬም ራሱን ከጣዖታት ጋር አጣምሮአል፤ብቻውን ተውት።
18አስካሪ መጠጣቸው ባላቀ ጊዜ እንኳን ማመንዘራቸውን አያቆ ሙም፤ገዢዎቿም ነውራቸውን እጅግ ይወዳሉ።
19ነፋሱ በክንፎቹ ይጠቀልላታል፥ ከመሥዋዕቶቻቸውም የተነሳ ይፍራሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።