1እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦«እንደገና ሂድ፥ ባልዋ የሚወዳትን ነገር ግን አመንዝራ የሆነችውን ሴት ውደድ። ወድ ሌሎች አማል ክት ዘወር ቢሉና የዘቢብ እንጎቻ ቢወዱም እንኳን፥ እኔ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ እንደምወድ ውደዳት።»
2ስለዚህ በአሥራ አምስት የብር ሳንቲሞችና በአንድ ቆሮስ ተኩል ገብስ ገዛኋት።
3እኔም፦ «ከእኔ ጋር ብዙ ቀናት ኑሪ፥ ሴተኛ አዳሪ ወይም የሌላ የማንም ሰው አትሁኚ፥እኔም እንዲዚሁ ከአንቺ ጋር እሆናለሁ» አልኳት።
4የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ፥ ያለ መስፍን፥ ያለ መሥዋዕት፥ ያለ ድንጋይ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድ ወይም ያለ ቤተሰብ ጣዖት ለብዙ ቀናት ይኖራሉ።
5ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሰዎች ይመለሳሉ፥ እግዚአብሔር አምላካቸውንና ንጉሣቸውን ዳዊትንም ይፈልጋሉ። በመጨረሻዎቹም ቀናት በእግዚአብሔርና በበረከቱ ፊት እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።