መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሆሴዕ 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ወንድሞቻችሁን «ሕዝቤ!»፥ እኅቶቻችሁንም «የተራራላችሁ» በሏቸው።
2እርሷ ሚስቴ አይደለችምና እኔም ባሏ አይደለሁምና ከእናታችሁ ጋር ተምዋግቱ፥ ተምዋገቱ። ሴተኛ አዳሪነቷን ከፊቷ፥ምንዝርናዋንም ከጡቶቿ መካከል ታስወግድ።
3አለበለዚያ እርቃንዋን እስክትቀር እገፋታልሁ፥እንደ ተወለደችበትም ቀን እርቃንዋን እገልጣለሁ። እንደ ምድረ በዳ እንደ ደረቅም ምድር አደርጋታለሁ፥ተጠምታ እንድትሞት አደርጋለሁ።
4የሴተኛ አዳሪነት ልጆች ናቸውና ለልጆቿ ቅንጣት ምሕረት የለኝም።
5ምክንያቱም እናታቸው ሴተኛ አዳሪ ናትና፥ የጸንሰቻቸውም በአሳፋሪ ተግባር ነውና። እርሷም ፦«እንጀራዬንና ውኃዬን፥ሱፌንና ሐሬን፥ዘይቴንና መጠጤን ይሰጡኛልና ከውሽሞቼ ኋላ እሄዳለሁ» አለች።
6ስለዚህ መንገድዋን በእሾህ ለመዝጋት አጥር እሠራለሁ። መንገድዋንም እንዳታግኝ ቅጥር እገነባባታለሁ።
7ውሽሞችዋን ትከታተላቸዋለች ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ትፈልጋቸዋለች ነገር ግን አታገኛቸውም። ከዚያም በኋላ ፦«አሁን ካለሁበት የበፊቱ ይሻላልና ወደ መጀመሪያው ባሌ እመለሳለሁ» ትላለች።
8እህሉን፥አዲሱን ወይን ጠጅና ዘይቱን የሰጠኋት፣ በአልን ያገለገሉበትን ብርና ወርቅ ያበዛሁላት እኔ እንደ ሆንኩ አላወቀችም።
9ስለዚህ እህሏን በመከር ጊዜ፥ አዲሱንም የወይን ጠጄን በወቅቱ መልሼ እወስዳለሁ። እርቃኗንም የምትሸፍንበትን ሱፌንና ሐሬን መልሼ እወስዳለሁ።
10ከዚያም ውሽሞችዋ እያዩ እርቃንዋን እስክትቀር ድረስ እገፋታለሁ፥ ከእጄም ማንም አያስጥላትም።
11ሁሉንም ክብረ በዓላቷን፦ የደስታ በዓላቷን፥የአዲስ ጨረቃ ክብረ በዓላቷን፥ ሰንበታቷንና ዓመታዊ በዓላቷን አስቀራለሁ።
12«ውሽሞቼ የሰጡኝ ክፍያዎቼ ናቸው» የምትላቸውን ወይንዋንና የበለስ ዛፎችዋን አጠፋለሁ። ጫካ አደርጋቸዋለሁ፥ የዱር አራዊትም ይበሉዋቸዋል።
13ለበአል አማልክት ዕጣን ስላጠነችባቸው፥ በቀለበቶችዋና በጌጣ ጌጦቿ ራስዋን ስላስዋበችባቸው እና እኔን ረስታ ከውሽሞቿ ኋላ ስልሄደችባችው የደስታ በዓላት እቀጣታለሁ።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
14ስለዚህ አመልሳታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳ እወስዳታለሁ፥ በፍቅርም አነጋግራታለሁ።
15የወይን ተክሏን፥ የተስፋ በርም እንዲሆናት የአኮርን ሸለቆ መልሼ እሰጣታለሁ። በዚያም በወጣትነቷ ቀናት፥ ከግብጽ ምድር በወጣችባቸው ቀናት እንዳደረገችው ትመልስልኛለች።
16የእግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፦«በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ ከእንግዲህ ወዲያም በአሌ ብለሽ አትጠሪኝም።
17የበአልን አማልክት ስም ከአንደበቷ አስወግዳለሁና ስሞቻቸው ከእንግዲህ ወዲያ አይታሰቡም።
18በዚያን ቀን ከዱር አራዊት፥ ከሰማይ አእዋፍና በምድር ከሚንቀሳቀሱት ነገሮች ጋር ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ። ቀስትን፥ ሰይፍንና ጦርነትን ክምድሪቱ አስወግዳለሁ፥ በሰላምም እንድትጋደሙ አደርጋችኋለሁ።
19ለዘላለም ባልሽ ልሆን ቃል እገባልሻለሁ። በጽድቅ፥ በፍትሕ፥ በኪዳን ታማኝነትና በምሕረት ባልሽ ልሆን ቃል እገባልሻለሁ።
20በታማኝነት ባልሽ ልሆን ቃል እገባልሻለሁ። አንቺም እኔን እግዚአብሔርን ታውቂያለሽ።
21የእግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፦ በዚያን ቀን እመልሳልሁ። «ለሰማያት እመልሳለሁ፥ እነርሱም ለምድር ይመልሳሉ።
22ምድርም ለእህሉ፥ ለአዲሱ ወይን ጠጅና ለዘይቱ ትመልሳለች፥ እነርሱም ለኢይዝራኤል ይመልሳሉ።
23ስለ ራሴ ስል በምድሪቱ ላይ እተክላታልሁ፥ ሎሩሃማንም እምራታለሁ። ሎዓሚንንም፦ አንተ ዓሚ አታህ ነህ እለዋለሁ፤ እነርሱም አንተ አምላካችን ነህ ይሉኛል።»
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።