መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሆሴዕ 13

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1«ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ መንቀጥቀጥ ነበረ። በእስራኤል መካከል ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ፥ ነገር ግን በአልን በማምለኩ በደለኛ ሆነ፥ ሞተም።
2አሁንም አብዝተው ኃጢአት ሠሩ። ከብራቸው የተቀረጸ ምስል ሠሩ፥ ጣዖታት በሚቻለው መጠን በጥበብ ተሠርተዋል፥ ሁሉም የባለ ሙያ ሥራ ናቸው። ሕዝቡ ስለ እነርሱ እንዲህ ይላሉ፦ 'እነዚህ የሚሠው ሰዎች ጥጃዎችን ይስማሉ።'
3ስለዚህ እንደ ማለዳ ደመና፥በጠዋት እንደሚጠፋ ጤዛ፥ከአውድማ ላይ በነፋስ እንደሚወሰድ እብቅ፣ከጪስ ማውጫ እንደሚወጣ ጢስ ናቸ ው።
4ነገር ግን ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር አምላክ አታውቅም፥ ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ አታውቅም።
5በምድረ በዳ፥ በታላቅም የድርቀት ምድር አውቅሁህ።
6መሰማሪያ ባገኘህ ጊዜ ጠገብህ፥ በጠገብህም ጊዜ ልብህ ታበየ፤ከዚህም የተነሳ ረሳኽኝ።
7እንደ አንበሳ ሆንኩባቸው፥እንደ ነብርም በመንገዳቸው አደባለሁ።
8ግልገሎቿን እንደ ተነጠቀች ድብ አጠቃቸዋለሁ። ደረታቸውን ቀድጄ ከፍታለሁ፥በዚያም እንደ አንበሳ እበላቸዋለሁ፥ እንደ ዱር አራዊትም እገነጣጥላቸዋለሁ።
9እስራኤል ሆይ በረዳትህ በእኔ ላይ ዓምፀሃልና ጥፋትህ እየመጣ ነው።
10በከተማዎችህ ሁሉ ያድንህ ዘንድ ንጉሥህ አሁን ወዴት ነው? ስለ እነርሱ፥ 'ንጉሥና መሳፍንቶች ስጠኝ' ብለህ የተናገርክላቸው፥ ገዢዎችህ ወዴት ናቸው?
11በቁጣዬ ንጉሥ ሰጠሁህ፥ በመዓቴም አስወገድኩት።
12የኤፍሬም ክፋት ተደብሮአል፥በደሉም ተደብሮአል።
13የምጥ ሕመም ይመጣበታል፥ እርሱ ግን ጥበብ የጎደለው ልጅ ነው፤ ምክንያቱም የሚወለድበት ጊዜ ቢደርስም ከማኅጸን አይወጣም።
14በእርግጥ ከሲዖል ኃይል አድናቸዋለሁን? በእርግጥ ከሞትስ አድናቸዋለሁን? ሞት ሆይ መቅሰፍቶችህ ወዴት አሉ? ወደዚህ አምጣቸው። ሲዖል ሆይ ማጥፋትህ ወዴት አለ? ወደዚህ አምጣው። ርህራኄ ከዓይኖቼ ተሰወረ።
15ኤፍሬም በወንድሞቹ መካከል ባለጸጋ ቢሆንም እንኳን፥ የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፤ የእግዚአብሔር ነፋስ ከምድረ በዳ ይነፍሳል። የኤፍሬም ምንጭ ይደርቃል፥ ጉድጓዱም ውኃ አይኖረውም። ጠላቱ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን ግምጃ ቤቱን ይበዘብዛል።
16በአምላኳ ላይ ዐምፃለችና ሰማሪያ በደለኛ ትሆናለች። በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ብላቴኖቻቸውም ይከሰከሳሉ፥ እርጉዝ ሴቶቻቸውም ይቀደዳሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።