መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሆሴዕ 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኤፍሬም ነፋስ ይመገባል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል። ሐሰትንና ዓመፅን ያለማቋረጥ ያበዛል። ከአሦር ጋር ኪዳን ያደርጋሉ፥ የወይራ ዘይትም ወደ ግብጽ ይወስዳሉ።
2እግዚአብሔር ከይሁዳ ጋር ሙግት አለው፥ ያዕቆብንም ስላደረገው ይቀጣዋል፥ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።
3ያዕቆብ በማሕፀን ውስጥ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፥ በጎልማስነቱም ከአምላክ ጋር ታገለ።ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ።
4አልቅሶም በፊቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለመነው። በቤቴል ከአምላክ ተገናኘ፥ በዚያም አምላክ ከእርሱ ጋር ተነጋገረ።
5እርሱም የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፤የሚጠራበት ስሙም «እግዚአብሔር» ነው።
6ስለዚህ ወደ አምላካችሁ ተመለሱ። ለኪዳኑ ታማኝነትን፥እንዲሁም ፍትሕን ጠብቁ፤ሁል ጊዜም አምላካችሁን ተስፋ አድርጉ።
7ነጋዴዎቹ ሐሰተኛ ሚዛኖችን በእጆቻቸው ይዘዋል፤ ማጭበርበርን ይወዳሉ።
8ኤፍሬምም፦ «በእርግጥ እጅግ ባለጠጋ ሆኜአለሁ፥ ሀብትንም አግኝቼአለሁ። በሥራዬ ሁሉ ኃጢአት የሚሆን ምንም ዓይነት በደል አያገኙብኝም» ይላል።
9ከግብጽ ምድር አንስቶ ከአናንተ ጋር የሆንኩ አምላካችሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። እንደ ዓመት በዓላት ቀናት ዳግመኛ በድንኳኖች እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ።
10ለነቢያቶቹም ተናገርሁ፥ ስለ እናንተም ብዙ ራዕዮችን ሰጠኋቸው። በነቢይቶቹም አማካይነት ምሳሌዎችን ሰጠኋችሁ።»
11በገለዓድ ኃጢአት ካለ፥ በእርግጥ ሕዝቡ ከንቱ ነው። በጌልጌላ ወይፈኖችን ይሰዋሉ፥ መሠዊያዎቻቸው በታረሰ መሬት ላይ እንዳለ የድ ንጋይ ክምር ይሆናሉ።
12ያዕቆብ ወደ ሶሪያ ምድር ሸሸ፤ እስራኤልም ሚስት ለማግኝት አገለገለ፥ ሚስትም ለማግኘት የበጎችን መንጋ ይጠብቅ ነበረ።
13እግዚአብሔር በነቢይ አማካይነት እስራኤልን ከግብጽ አወጣ፥ በነቢይም አማካይነት ተጠነቀቀለት።
14ነገር ግን እግዚአብሔር ይቆጣ ዘነድ ኤፍሬም ክፉኛ አነሳሳው። ስለዚህ ጌታው የደሙን በደል በእርሱ ላይ ይደርጋል፥ አሳፋሪም ስለ ሆነው ሥራው የሚገባውን ይከፍለዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።