1እስራኤል ሆይ ከክፋትህ የተነሳ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።
2የኑዛዜ ቃላት ያዝና ወደ እግዚአብሔር ተመለስ። እንዲህም በሉት፦«የከንፈሮቻችንን ፍሬ ምስጋናችንን እንሰዋልህ ዘንድ፤ክፋታችንን አስወግድ፥በቸርነትም ተቀበለን።
3አሦር አያድነንም፤ ለጦርነትም ፈረሶችን አንጋልብም። ወይም ከእንግዲህ የእጆቻችንን ሥራዎች 'እናንተ አምላኮቻችን ናችሁ' አንላቸውም፤ አባት አልባው እንኳ በአንተ ዘንድ ርኅራኄን ያገኛልና።
4ከተውኝም በኋላ ወደ እኔ በተመለሱ ጊዜ እፈውሳቸዋለሁ፤ እንዲያው እወዳቸዋለሁ፥ ቁጣዬ ከእርሱ ተመልሶአልና።
5እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤ እንደ አበባ ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ዝግባ ሥር ይሰዳል።
6ቅርንጫፎቹ ይዘረጋሉ፤ ውበቱ እንደ ወይራ ዛፎች፥ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ዝግባዎች ይሆናል።
7ከጥላው በታች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ይመለሳሉ፤እንደ እህል ይለመልማሉ፥ እንደ ወይንም ያብባሉ።ዝናውም እንደ ሊባኖስ ወይን ጠጅ ይሆናል።
8ኤፍሬም፦ 'ከእንግዲህ ከጣዖታት ጋር ምን አለኝ?' ይላል። እኔ እመልስለታለሁ፥እጠነቀቅለታለሁም። እኔ ቅጠሎቹ ሁል ጊዜ ለመለም እን ደሆኑ እንደ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህም ከእኔ ይመጣል።»
9እነዚህን ነገሮች ያስተውል ዘንድ ጠቢብ የሆነ ማን ነው? ያውቃቸው ዘንድ እነዚህን ነገሮች የሚያስተውል ማን ነው? የእግዚአብሔር መንገዶች ትክክል ናቸው፥ ጻድቃንም ይሄዱባቸዋል፥ ዓመፀኞች ግን ይሰናከሉባቸዋል።