መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሆሴዕ 11

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እስራኤል ወጣት በነበረበት ጊዜ ወደድኩት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።
2አብዝቶ በተጠሩ መጠን፥ አብዝተው ራቁ። ለበአል አማልክት ሠው፥ ለጣዖታትም አጠኑ።
3ሆኖም ግን ኤፍሬምን መራመድ ያስተማርኩት እኔ ነበርኩ። ክንዶቻቸውን ይዤ ያነሳኋቸው እኔ ነበርኩ፥ እነርሱ ግን የተጠነቀቅሁላቸው እኔ እንደሆንሁ አላወቁም።
4በሰው ገመድ፥ በፍቅርም ማሰሪያ መራኋቸው። የመንጋጋዎቻቸውን ማሰሪያ እንደሚያላላ ሆንኩላቸው፥ ዝቅ ብዬም መገብኳቸው።
5ወደ ግብጽ ምድር አይመለሱምን? ወደ እኔ መመለስን እምቢ በማለታቸው አሦር አይገዛቸውምን?
6ሰይፍ በከተሞቻቸው ላይ ይወድቃል፥ የበሮቻቸውንም መቀርቀሪያ ያጠፋል፤ከገዛ ራሳቸው ዕቅድ የተነሳ ያጠፋቸዋል።
7ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ለማለት ቆርጦአል። በከፍታ ወደ አለሁት ወደ እኔ ቢጣሩ እንኳ፥ማንም አይረዳቸውም።
8ኤፍሬም ሆይ እንዴት እተውሃለሁ? እስራኤል ሆይ እንዴት አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዮ አደርግሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተለውጦአል፤ መላው ርኅራኄዬ ተነሣሥቷል።
9ጽኑ ቁጣዬን አላመጣም፤ ኤፍሬምን ዳግመኛ አላጠፋም። እኔ አምላ ክ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥በመካከልህ ቅዱሱ ነኝና፥በቁጣ አልመጣም።
10እነርሱም ከእኔ ከእግዚአብሔር በኋላ ይመጣሉ። እንደ እንበሳ አገሳለሁ። በእርግጥ አገሳለሁ፥ ሕዝቡም ከምዕራብ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።
11ከግብጽ እንደ ወፍ፥ ከአሦርም ምድር እንደ ርግብ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ። በየቤቶቻቸውም አኖራቸዋለሁ።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
12«ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤልም ቤት በማታለል ከበበኝ። ይሁዳ ግን እስካሁን ከእኔ ከአምላኩ ጋር ጸንቷል፥ ለእኔም ለቅዱሱ የታመነ ነ ው።»
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።