መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዕብራዊያን 8

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እንግዲህ ልንናገር የፈለግነው ጉዳይ ዋና ነጥቡ ይሄ ነው፦ በሰማያት በልዑል እግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ ሊቀ ካህን አለን።
2እርሱ እግዚአብሔር በተከላት እውነተኛይቱ የማደሪያ ድንኳን፣ በተቀደሰው መቅደስ አገልጋይ የሆነ ነው እንጂ ማንኛውም ሟች ሰው አይደለም።
3ማንኛውም ሊቅቀ ካህናት የሚሾመው ስጦታዎችንና መሥዋዕቶችን ለማቅረብ በመሆኑ፣ የሚቀርብ ነገር ይዞ መገኘት አስፈላጊ ነው።
4ታዲያ ክርስቶስ አሁን በምድር ላይ የሚኖር ቢሆን በሕጉ መሠረት ስጦታዎችን የሚያቀርቡ ስላሉ እርሱ በፍጹም ካህን መሆን ባልቻለም ነበር።
5የማደሪያ ድንኳኑን ለመሥራት በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን”አስተውል፣ በተራራው ላይ ባየኸው ምሳሌ መሰረት ማንኛውንም ነገር እንድትሠራ” በማለት እንዳስጠነቀቀው ሁሉ እነርሱ የሰማያዊ ነገሮች ጥላና ግልባጭ የሆኑ ነገሮችን የሚያገለግሉ ናቸው።
6ነገር ግን በተሻለ ተስፋ ላይ የተመሠረተ የተሻለ ኪዳን መካከለኛው በመሆኑ ክርስቶስ አሁን የላቀ አገልግሎት ተቀብሏል።
7ያ የመጀመሪያው ኪዳን ነቀፋ ካልነበረው ሁለተኛ ኪዳን የሚፈለግበት ምንም ምክንያት አይኖርም ነበር።
8እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ነቀፋ ባገኘ ጊዜ እንደዚህ ብሎ ነበርና”አስተውሉ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ዘመን ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር።
9“ከግብፅ ምድር በእጆቼ መርቼ ባወጣኋቸው በዚያን ዘመን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት እንደዚያ ቃል ኪዳን አይሆንም። በዚያ ኪዳኔ አልጸኑምና እኔም ችላ አልኳቸው” ይላል እግዚአብሔር።
10“ከእነዚያ ዘመናት በኃላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ይህንን ኪዳን ነው፥ ‘ሕጌን በልቦናቸው አኖራለሁ፣ በልቦቻቸውም ላይ እጽፈዋለሁ። አምላካቸው እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
11እያንዳንዱ ጎረቤቱን እያንዳንዱም ወንድሙን፥ ‘እግዚአብሔርን እወቅ እያለ አያስተምርም፣ እጅግ ታናሽ ከሆነው ጀምሮ እጅግ ታላቅ እስከሆነው ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና።
12በዓመፅ ለፈጸሟቸው ድርጊቶች ሁሉ ምሕረት አደርጋለሁና ኃጢአቶቻቸውንም ከእንግዲህ አላስብምና”
13‘አዲስ’ በማለቱም የመጀመሪያው ኪዳን አስረጅቷል። አሮጌ ነው ብሎ የገለጸውም ሊወገድ ተቃርቧል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።