1የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የነበረው ይህ መልኬ ጼዴቅ የባረከው አብርሃምን ነገሥታቱን ድል አድርጎ ሲመለስ ነበር።
2አብርሃምም ከማረጀው ከማንኛውም ነገር አንድ አሥረኛውን ለእርሱ ሰጠው። ‘መልኬ ጼዴቅ’ የሚለውም የስሙ ትርጉም ‘የጽድቅ ንጉሥ’ ደግሞም ‘የሳሌም ንጉ’ ማለትም ‘የሰላም ንጉሥ’ ማለት ነው።
3እርሱ አባትም ሆነ እናት፣ የትውልድ ሐረግም ሆነ የጅማሬ ወይም የፍጻሜ አመን የሌለው ነው። ይልቁንም እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሁሉ እርሱም ካህን ሆኖ ለዘላለም ይኖራል።
4ይህ ሰው እንግዲህ ምን ያህል ታላቅ እንደነበረ አስቡ። አባታችን አብርሃም በጦርነት ካገኛቸው ምርጥ ነገሮች አንድ አሥረኛ የሚሆነውን ሰጥቶታል።
5በእርግጥ የክህነቱን አገልግሎት የተቀበሉትም የሌዊ ዝርያዎች ከአብርሃም ዝርያ የተገኙ ቢሆኑም ከሕዝቡ ማለትም ከእስራኤላውያን ወገኖቻቸው አሥራትን ይሰበስቡ ዘንድ በሕጉ ታዘዋል።
6ይሁን እንጂ የሌዊ ዝርያ ያልነበረው መልኬ ጼዴቅ የተስፋ ቃሎች ከነበሩት ከአብርሃም አሥራትን ተቀበለ፣ ባረከውም።
7ታናሹ በታላቁ እንደሚባረክ የሚካድ ነገር አይደለም።
8በአንድ በኩል ስናየው አሥራትን የሚቀበሉ ሰዎች አንድ ቀን ይሞታሉ በሌላ በኩል ስንመለከተው ግን ከአብርሃም አሥራትን የተቀበለው ሕያው ሆኖ እንደሚኖር ተገልጿል።
9በሌላ አነጋገር አሥራትን ይቀበል የነበረው ሌዊ እንኳን በአብርሃም በኩል አሥራትን ሰጥቷል።
10ምክንያቱም መልኬ ጼዴቅ አብርሃምን ባገኘው ጊዜ ሌዊ በቀደምት አባቱ በአብርሃም አብራክ ውስጥ ነበረና።
11ሕዝቡ ሕጉን የተቀበሉት በዚህ ሥርዓት በነበሩ ጊዜ ነበርና ፍፁምና በሌዊ ክህነት ማግኘት የሚቻል ቢሆን ኖሮ በአሮን ሥርዓት ሳይሆን በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት የሚሾም ሌላ ካህን ወደፊት ይነሳ ዘንድ ምን ያስፈልግ ነበር?
12ክህነቱ የሚለውጥ ከሆነ ደግሞ ሕጉም መለወጥ ይገባዋል።
13እነዚህ ነገሮች እየተነገሩለት ያለው ከወገኖቹ ከቶ ማንም በመሠዊያው ላይ አገልግሎ የማያውቅ የሌላ ነገድ ወገን ነውና።
14እንግዲያውስ ጌታችን ካህናትን በሚመለከት ሙሴ ከቶውንም ምንም ካልተናገረለት ከይሁዳ ነገድ የመጣ መሆኑ ግልጽ ነው።
15መልከ ጼዴቅን የመሰለ ሌላ ካህን ቢነሳ የምንለው ይበልጥ ግልጽ ይሆናል።
16ይሄኛው ካህን ደግሞ ሰብዓዊ ዝርያን መሠረት በሚያደርገው ሕግ ሳይሆን የማይጠፋ የሕይወት ያይልን መሠረት ባደረገ ሕግ ካህን የሆነ ነው።
17ቅዱሳት መጻሕርትም ስለ እርሱ እንዲህ ሲሉ ይመሰክራሉ፦ “በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ”
18የቀደመው ትዕዛዝ ገለል የተደረገው ደካማና የማይጠቅም በመሆኑ ነውና።
19ሕጉ ፍጹም ያደረገው ምንም ነገር አልነበረምና። ይሁን እንጂ ከዚህ በኃላ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የተሻለ መተማመኛ አለ።
20ይሄኛው የተሻለው መተማመኛ ግን ያለ መሃላ እውን አልሆነም፣ ምክንያቱም እነዚህ ሌሎቹ ካህናት ምንም መሃላ አልፈጸሙም።
21“ጌታ ምሎአል ሃሳቡንም አይቀይርም፤ ‘አንተ ለዘላለም ካህን ነህ’” ተብሎ እንደተጻፈ።
22በዚህም ደግሞ ኢየሱ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።
23በእርግጥም ሞት ካህናቱን ለዘላለም ከማገልገል ያግዳቸዋል። እብንዱ ሌላውን እየተካ፣ ካህናት የሆኑት የበዙት ከዚህ የተነሣ ነው።
24ኢየሱስ ግን ለዘላለም ስለሚኖር የእርሱ ክህነት የማይለወጥ ነው።
25ስለዚይ ስለ እነርሱ ሊማልድ ምን ጊዜም በሕይወት ስለሚኖር በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሙሉ በሙሉ ሊያድናቸው ይችላል።
26እንደዚህ ያለው ማለትም ኃጢአትና ነቀፋ የሌለበት፣ ንጡሕ፣ ከኃጢአተኞች የተለየ ከሰማያትም በላይ ከፍ ያለ ሊቀ ካህን ሊኖረን ይገባል።
27እርሱ ሊቀ ካህናቱ ሲያደርጉት እንደነበረው በመጀመሪያ ራሱ ለሠራቸው ኃጢአቶች ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ለፈፀሟቸው ኃጢአቶች በየቀኑ መሥዋዕቶችን ማቅረብ አያስፈልገውም። ራሱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ይህንን ለአብዴና ለመጨረሻ ጊዜ አድርጎታል።
28ሕጉ ድካም ያለባቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፣ ከሕጉ በኃላ የመጣው የመሐላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የተደረገውን ልጁን ሾሟልና።