1እያንዳንዱ ሊቀ ካህን ከሰዎች መካከል ይመረጣል፤ ለኃጢአት መሥዋዕትንና መባን ለማቅረብ እግዚአብሔርን በሚመለከት ጉዳይ እነርሱን በመወከል ይሾማል።
2እርሱ ራሱም በድካም ውስጥ ያለ በመሆኑ ዐላዋቂዎችንና ከመንገድ የሳቱትን ሊራራላቸው ሊቀበላቸው ይችላል።
3ከዚህም የተነሣ ለሕዝቡ ኃጢአት እንደሚያድርገው ሁሉ እርሱም ለገዛ ራሱ ኃጥአት መሥዋዕት ማቅረብ ይኖርበታል።
4እንደ አሮን በእግዚአብሔር የተጠራ ካልሆነ በቀር ማንም ይህን ክብር በራሱ አያገኘውም።
5ክርስቶስ ራሱም ቢሆን ሊቀ ካህናት የመሆንን መብት በገዛ ራሱ አልወሰደም። ይልቁንም እግዚአብሔር ለእርሱ፣
6ይህም በሌላ ቦታ፣ እግዚአብሔር፣እንደመልከጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ" ይላል።
7ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በነበረ ዘመን ፣ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ። እግዚአብሔርን በመፍራቱም ጸሎቱ ተሰማለት።
8ምንም እንኳ እርሱ ልጅ ቢሆንም፣ ከደረሰበት መከራ የተነሣ መታዘዝን ተማረ።
9በዚህ ሁኔታ ሁሉ የዘላለም ድነት ምክንያት ሆነላቸው፤
10እግዚአብሔርም እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት አድርጎ ሾመው።
11ስለ ኢየሱስ ብዙ የምንናገረው አለን፤ ሆኖም፣ ለመቀበል ዳተኞች ስለሆናችሁ፣ ለእናንተ ማስረዳት አዳጋች ነው።
12እስከ አሁን ድረስ መምህራን መሆን ሲገባችሁ፣ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረታዊ መርሖዎች የሚያስተምራችሁ ሰው ገና ትፈልጋላችሁ። እናንተ የምትፈልጉት ወተት እንጂ፣ ጠንካራ ምግብ አይደለም።
13ወተት ብቻ ሊጋት ማንኛውም ሰው ገና ሕፃን ስለሆነ የጽድቅ ትምህርት ልምምድ የለውም።
14በሌላ በኩል ደግሞ ጠንካራ ምግብ ግን መልካምንና ክፉውን መለየት ለተማሩና ትክክል የሆነውን ካልሆነው የመለየት ልምድ ላላቸው ትልልቅ ሰዎች ነው።