መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዕብራዊያን 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ዕረፍት ከሆነው ዘላቂ ተስፋ የሚጎድል እንዳይመስለው በጣም መጠንቀቅ አለብን።
2ምክኒያቱም ለእስራኤላውያን እንደ ተነገረ ሁሉ ለእኛም ስለ እግዚአብሔር ዕረፍት መልካም ዜና ተነግሮናል፤ ሆኖም፣ የሰሙትን መልእክት ሰሞዎቹ በእምነት ስላልተቀበሉት አልጠቀማቸውም።
3“ወደ ዕረፍቴ አይገቡም፣ ብዬ በቁጣዬ ማልሁ” እንዳለው ሳይሆን እኛ ያመንን ግን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን። የእርሱ ፍጥረት ሥራ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣
4ስለ ሰባተኛ ቀን በማመልከት አንድ ቦታ “በሰባተኛው ቀን እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ዐረፈ” ይላል።
5ደግሞም፣ “ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ይላል።
6ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት ለመግባት ለአንዳንዶች አሁንም የተጠበቀባቸው በመሆኑና ፣ መልካሙን ዜና ከሰሙት እስራኤላውያን ብዙዎቹ ባለ መታዘዛቸው ምክንያት ወደ ዕረፍቱ ባለ መግባታቸው እግዚአብሔር በድጋሚ፣
7“ዛሬ” የተባለ ቀን ወስኖአል።
8ኢያሱ አሳርፎአቸው ቢሆን ኖሮ፣ እግዚአብሔር ስለ ሌላ ቀን አይናገርም ነበር።
9ስለዚህ ለእግዚአብሔር ሕዝብ አሁንም ቢሆን የሰንበት ዕረፍት ተጠብቆላቸዋል።
10ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት የገባ ሰው እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ ሁሉ፣ እርሱም ከሥራው ያርፋል።
11ስለዚህ ማንም የእነዚያን ሰዎች ዐመፅ ተከትሎ እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንናፍቅ።
12የእግዚአብሔር ቃል ሕያው፣ የሚሠራና፣ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ፣ ስለታም ነው። ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ ይወጋል። የልብን ሐሳብና ውስጥን ይመረምራል።
13ከእግዚአብሔር ፊት የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም። እኛ ተጠያቂዎች በሆንንበት በእርሱ ዓይኖች ፊት ማንኛውም ነገር የተገለጠና የተራቆተ ነው።
14እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ።
15ነገር ግን እርሱ ከኃጢአት በቀር በማንኛውም ነገር እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንምና።
16ስለዚህ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትንና የሚረዳንን ጸጋ እንድንቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።