መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዕብራዊያን 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ስለዚህ የሰማያዊ ጥሪ ተከፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች የእምነታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን አስቡ።
2ሙሴ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ ታማኝ እንደ ነበር ሁሉ፣ እርሱም ለሾመው ለእግዚአብሔር ታማኝ ነበር።
3ቤቱን የሚሠራው ከራሱ ከቤቱ የበለጠ ክብር እንዳለው ሁሉ፣ ኢየሱስም ከሙሴ ይልቅ የበለጠ ክብር እንደሚገባው ተቆጥሯል።
4ማንኛውም ቤት ሠሪ አለው፤ ሁሉም ነገር የሠራ ግን እግዚአብሔር ነው።
5ወደ ፊት መነገር ለሚገባው ነገር ምስክር እንዲሆን፣ ሙሴም በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ እንደ አገልጋይ ታማኝ ነበር።
6ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ሥልጣን ያለው ልጅ ነው። የምንተማመንበትንና የመተማመናችንን ድፍረት አጥብቀን ብንይዝ ቤቱ ነን።
7ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ፣ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ
8በምድረበዳ በፈተና ቀን በአመጽ እንዳደረጋችሁት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።
9ይህ የሆነው አባቶቻችሁ እኔን በመፈታተን ሲያምፁብኝና ዐርባ ዓመት ሙሉ ሥራዎቼን ባዩበት ጊዜ ነበር።
10ስለዚህ በዚያ ትውልድ ደስ አልተሰኘሁም። እንዲህም አልኩ፤ ልባቸው ሁል ጊዜ ይስታል መንገዴንም አላወቁም።
11ስለዚህ በቁጣዬ፥ "ወደ እረፍቴ አይገቡም" ብዬ ማልሁ።
12ወንድሞች ሆይ ከእናንተ ማንም የማያምን ክፉና ከሕያው እግዚአብሔር ዘወር የሚል ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።
13ይልቁንስ ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልኸኛ እንዳይሆን ከዛሬ ጀምሮ በየዕለቱ እርስ በርሳችሁ ተበረታቱ።
14ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ በእርሱ ያለንን ድፍረት አጥብቀን ከያዝን ከክርስቶስ ጋር ተባባሪዎች እንሆናለን።
15ስለዚህም፣ "ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ በአመጽ ጊዜ እንደሆነው ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ" ተብሏል።
16ለመሆኑ፣እነዚያ ድምፁን ሰምተው ያመፁት እነማን ነበሩ? ሙሴ እየመራ ከግብፅ ያወጣቸው ሁሉ አይደሉምን?
17ለአርባ ዓመት እግዚአብሔር የተቆጣባቸውስ እነማን ነበሩ? ኃጢአት ያደረጉና ሬሳቸው በበረሃ ወድቆ የቀረው አይደሉምን?
18ደግሞስ እነዚያ ያልታዘዙት ካልሆኑ በቀር ወደ ዕረፍቱ እንደማይገቡ እግዚአብሔር የማለባቸው እነማን ሊሆኑ ነው?
19ባለማመናቸው ምክንያት ወደ ዕረፍቱ ሊገቡ እንዳልቻሉ እናያለን።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።