መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዕብራዊያን 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ስለዚህ ከሰማነው ነገር እንዳንወሰድ፣ ስለ ሰማነው ነገር ይበልጥ መጠንቀቅ አለብን።
2በመላእክት አማካይነት የመጣው መልእክት ጽኑ ከሆነና፣ ማንኛውም መተላለፍና ዐመፅ ተገቢውን ቅጣት የሚቀበል ከሆነ።
3ታዲያ፣ይህንን ታላቅ መዳን ቸል ካልን እንዴት ማምለጥ እንችላለን?
4እግዚአብሔርም ምልክቶችን፣ ድንቆችንና የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ፣እንደ ፈቃዱ በታደሉት በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አማካይነት ምስክርነታቱን አጽንቶአል።
5ይህ እየተናገርንለት ያለውን ወደ ፊት የሚመጣውን ዓለም እግዚአብሔር ለመላእክት አላስገዛም።
6እንዲያውም በቅዱሳት መጻህፍት አንድ ሰው አንድ ስፍራ ሲናገር፣
7ሰውን ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንህለት።
8ማንኛውንም ነገር ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት” ብሏል። እግዚአብሔር ከእግሩ በታች ሲያስገዛለት ምንም ያላስገዛለት ነገር የለም። ነገር ግን በእሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት ገና አናይም።
9ይሁን እንጂ፣ ከመከራውና ከሞቱ የተነሣ ከመላእክቱ በጥቂቱ አንሶ የነበረውን ኢየሱስ፣ የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖለት እናያለን። በእግዚአብሔር ጸጋ እርሱ ለሰው ሁሉ ሞትን ቀምሷል።
10ሁሉም በእርሱና ለእርሱ የሚኖር ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት የድነታቸውን መሥራች በመከራው አማካይነት እግዚአብሔር ፍጹም ሊያደርገው ተገቢ ሆነ።
11የሚቀድሰውም ሆነ የሚቀደሱት ሁለቱም ከአንዱ ምንጭ፣ ከእግዚአብሔር ናቸው። በዚህም ምክንያት የሚቀድሳቸው እርሱን ወንድሞቼ ብሎ ሊጠራቸው አላፈረም።
12እንዲያውም፣
13እንዲሁም፣ “እኔ በእርሱ እታመናለሁ” ይላል። በተጨማሪ፣ “እነሆ እኔንና እግዚአብሔር የሰጠኝን ልጆች ተመልከቱ” ብሏል።
14ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በሥጋና ደም ስለሆኑ፣ በሞቱ አማካይነት ሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ማለትም ዲያብሎስን ለመሻር ኢየሱስም እንደ እነርሱ ሥጋ ለብሶ።
15ይህም የሆነው ዕድሜ ልካቸውን በሞት ፍርሃት ምክንያት ዕድሜ ልካቸውን ባርነት ውስጥ የነበሩትን ሁሉ ነጻ ለማውጣት ነው።
16እርግጥም እየረዳቸው ያለው መላእክትን ሳይሆን፣ የአብርሃም ዘሮችን ነው።
17ስለሆነም የእግዚአብሔር በሆነ ነገር ሁሉ መሓሪና ታማኝ ሊቀ ካህን ለመሆንና ለሰዎችም ሁሉ የኃጢአት ይቅርታን ለማስግገኘት በሁሉም ረገድ ወንድሞችን መምሰሉ አስፈላጊ ሆነ።
18ኢየሱስ ራሱ መከራ የተቀበለና የተፈተነ በመሆኑ፣ የሚፈተኑትን ሁሉ ሊረዳቸው ይችላል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።